Saturday, 13 March 2021 12:18

የረ/ፕ ደረጀ ገብሬ “መራሄ ንባብ” መፅሐፍ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(2 votes)

   በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት ረ/ፕ ደረጀ ገብሬ “መራሄ ንባብ” መፅሐፍ መጋቢት 11 ቀን 2013 ዓ.ም በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ከረፋድ 4፡00 ጀምሮ ይመረቃል።
ዋና ትኩረቱን በንባብ ችሎታ ማዳበር ላይ ያደረገው መፅሐፉ የማንበብ ክሂል ማበልፀጊያና ሌሎች 10 ለልጆች የቀረቡ ትረካዎች  የተሰኙ መፅሐፎች በዚሁ ዕለት እንደሚመረቁም ታውቋል። “መራሄ ንባብ” የተሰኘው ይህ መፅሐፍ በተለይ ለአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በመምህራን ደጋፊነትና በወላጆች ተባባሪነት ወደ ላቀ ክህሎት እንዲደርሱ መንገድ ይጠርጋ ተብሏል። በ220 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ በ160 ብር ለገበያ ቀርቧል።

Read 3079 times