Saturday, 13 March 2021 12:21

“የአድዋ ጦርነትና የዓለም ቅኝ ግዛት አሰላለፍ” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በኤርሚያስ ጉልላት የተዘጋጀውና “የዓድዋ ጦርነትና የዓለም ቅኝ ግዛት አሰላለፍ” የተሰኘው መፅሐፍ ለንባብ በቃ።
መፅሐፉ በዋናነት የዓድዋ ጦርነትና በጦርነቱ የተገኘው ድል የዓለም የጥቁር ህዝቦች ህዝብ ድል መሆኑን፣ ከአድዋ ጦርነት በኋላ ስለጨነገፈው የአውሮፓውያን የቅኝ ግዛት መስፋፋት፣ አውሮፓውያንን አፍሪካን ቅኝ ለመግዛት የተስማሙበት የበርሊን ጉባኤ መፈረካከስና የነጭ የበላይነት እንዴት በጥቁር እንደሚረታ የታየበት ስለመሆኑ የወቅቱን የቅኝ ግዛት አስተላለፍና ከአድዋ ጦርነት በኋላ ስለ ከሸፈው የቅኝ ገዢዎች ህልም በስፋት ይተነትናል። በ13 ዋና ዋና ክፍሎች ተደራጅቶና አስረጂ ፎቶ-ግራፎችን ጨምሮ በ307 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ በ300 ብር  ለገበያ የቀረበ ሲሆን፣ “እነሆ” መፅሐፍት መደብር በዋናነት እያከፋፈለው ይገኛል።

Read 11276 times