Saturday, 20 March 2021 11:20

የምርጫ ጉዳዮችን ብቻ የሚዳኙ 21 ችሎቶች ተደራጅተዋል

Written by  መታሰቢያ ካሣዬ
Rate this item
(0 votes)

 በመጪው ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 ቀን 2013 የሚካሄደውን ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ፣ የሚነሱ ቅሬታዎችንና ውዝግቦችን የሚዳኙ 21 ችሎቶች መደራጀታቸው ተገለፀ።
በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የህግ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የምርጫ ጉዳዮች የሚስተናገዱበትን ስነ-ስርዓት በተመለከተ ከህግ ባለሙያዎች ጋር ትናንት ውይይት አካሂዷል።
በዚሁ ውይይት ላይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዚዳንትና የፌደራል ፍ/ቤቶች ቃል-አቀባይ አቶ ተስፋዬ ንዋይ እንደተናገሩት፤ መጪውን አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ የምርጫ ጉዳዮችን ብቻ የሚዳኙ 10 ችሎቶች በከፍተኛ ፍ/ቤት፣ 11 ችሎቶች ደግሞ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ስር ተደራጅተዋል ብለዋል።
እያንዳንዳቸው ችሎቶች 3 ዳኞች የሚኖራቸው ሲሆን ችሎቶቹ በምርጫ እጩ ምዝገባ፣ በመራጮች ምዝገባ፣ በድምፅ አሰጣጥና በውጤት አገላለፅ ሁኔታዎች ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን ይዳኛሉ ተብሏል።


Read 869 times