Saturday, 27 March 2021 13:07

7ኛው ጉማ አዋርድ ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  አርቲስት ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) የህይወት ዘመን ተሽላሚ ይሆናሉ

              በየአመቱ በፊልምና በፊልም ሙያ ዙሪያ የላቀ ስራ የሰሩትን እያወዳደረ የሚሸልመው “ጉማ ፊልም ሽልማት” ሰባተኛው ዙር ሽልማት ዛሬ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል በሰማያዊ ምንጣፍ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል።
በዚህ ሽልማት በ2011 ዓ.ም ተሰርተው በኮቪድ ምክንያት ሽልማቱ ባለመካሄዱ ለውድድር ያልቀረቡና በ2012 ዓ.ም ተሰርተው መስፈርቱን ያሟሉ 45 ፊልሞቹ ለውድድር መቅረባቸውን የጉማ አዋርድ መስራችና ዋና ዳይሬክተር አርቲስት ዮናስ ብርሃነ መዋ ገልጿል። ዘንድሮ በ19 ዘርፍ እጩዎች የሚሸለሙ ሲሆን ዘርፎቹም ምርጥ ፊልም ፣ ምርጥ ቅንብር፣ ምርጥ ድምጽ ፣ ምርጥ ዋና ወንድ ተዋናይ፣ ምርጥ ዋና ሴት ተዋናይት፣ የበደሌ ስፔሻል ምርጥ የህዝብ ምርጫ ፊልም፣ ምርጥ ዳይሬክተር ፣ ምርጥ  የፊልም ጽሁፍ ፣ ምርጥ ስኮር ፣ምርጥ ረዳት ሴት ተዋናይት፣ ምርት ረዳት ወንድ ተዋናይ፣ ምርጥ  ተስፋ የተጣለባት ሴት ተዋናይት፣ ምርጥ ተስፋ የተጣለበት ወንድ ተዋናይ፣ ምርጥ አጭር ፊልም፣ ምርጥ ሲኒማቶግራፊ፣ ምርጥ የፊልም ሙዚቃና ምርት ገጽ ቅብ (ሜካፕ) ሲሆኑ የክብር ዶክተር አርቲስት ተስፋዬ አበበ በህይወት ዘመን ተሸላሚነት ተመርጠዋል።
በየዘርፉ አምስት አምስት ለመጨረሻ ዙር ያለፉ ፊልሞችና ሙያተኞች የተለዩ ሲሆን ዛሬ ከቀኑ 11፡00 ተዋንያን፣ የፊልም አፍቃሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች በተገኙበት ሽልማቱ ይካሄዳል ተብሏል። በስነ-ስርዓቱ ላይ ለመታደም በሽልማት ድርጅቱ የሚፈቀደውን የአለባበስ ስርዓት መከተል ተገቢ እንደሆነም ታውቋል።

Read 11159 times