Saturday, 27 March 2021 12:32

“ሀገር ምን ትሻለች” የኪነ-ትበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን በየወሩ የሚዘጋጀው የኪነ-ጥበብ ምሽት የዚህ ወር መሰናዶ “ሀገር ምን ትሻለች” በሚል ርዕስ ከነገ በስቲያ መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሄራዊ ቴአትር ይካሄዳል።
በእቱ ዲስኩር፣ ወግ፣ ግጥምና ሙዚቃ ለታዳሚ የሚቀርብ ሲሆን በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር፣ ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም፣ ተስፋዬ እሸቱ (ረ/ፕ)፣ ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ፣ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ አቶ ዛዲግ አብርሃ፣ ገጣሚ ቴዎብስታ ምንዳዬ፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ በለጠ ሞላ (ረ/ፕ) እና ገጣሚ ማርታ  ተስፋዬ ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።
 ሙዚቃና ድራማ  የዝግጅቱ  አካል ሲሆኑ የመግቢያ ዋጋ 100 ብር ነው።

Read 849 times