Saturday, 03 April 2021 18:15

ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች የኮቪድ ክትባት ሊስጥ ነው

Written by  መታሰቢያ ሳሣዬ
Rate this item
(2 votes)

 ዕድሚያቸው ከ65 ዓመት በላይ ለሆናቸውና እድሚያቸው ከ55 አስከ 64 ዓመት ድረስ ሆኖ ተጓዳኝ የጤና ችግር ላለባቸው ሰዎች ከሰኞ ጀምሮ የኪቪድ 19 መከላከያ ክትባት ሊሰጥ ነው፡፡ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ሰሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፤ መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም በአገራችን በጤና ባለሙያዎች የተጀመረው የኮቪድ-19 ክትባት አሁን ዕድሚያቸው ለገፉትና ተያያዥ የጤና ችግሮች ላለባቸው ወገኖች ለመስጠት ዝግጅቱ ተጠናቋል ብለዋል፡፡ በመጪው ሰኞም ከ65 ዓመት በላይ ለሆናቸውና ከ55 ዓመት በላይ ሆነው ተያያዥ የጤና ችግሮች እንዳለባቸው ማስረጃ ለሚያቀርቡ ሰዎች ይሰጣል ብለዋል፡፡
ዕድሚያቸው ከ65 ዐኣመት የሆናቸው ሰዎች የቀበሌ መታወቂያ በመያዝ እንዲሁም ተጓዳኝ የጤና ችግር ኖሮባቸው እድሚሜያቸው 55 ዓመት የሆናቸው ሰዎች ደግሞ ክትትል ወደ ሚያደርጉበት የጤና ተቋም በመሄድ እንዲመዘገቡና ክትባቱን መውሰድ እንዲጀምሩ ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የጤና ሚኒስቴር ክትባቱ በቅድሚያ ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በደረጃ ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የገለፁት ሚኒስትሯ በቀጣይም እንደ ሁኔታው አስቸኳይነት- እንደቅድሚያ አፈላለጉ እየታየ ክትባቱ ለሌሎች ዜጎች እንዲዳረስ ያደርጋል ብለዋል፡፡ ክትባቱና የበሽታውን ስርጭት ለመግታትና በወረርሽኙ ሳቢያ የሚከሰተውን ፅኑ ህመምና ሞት ለመቀነስ የሚያግዝ ቢሆንም ህብረተሰቡ ራሱን ከበሽታው ሊከላከል ከሚችልበት የጥንቃቄ እርምጃ ለአፍታም ቢሆን ሊዘናጋ አይገባም ብለዋል፡፡


Read 9850 times