Print this page
Saturday, 03 April 2021 18:34

“ለምን?” መፅሀፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በተለያየ የመንግስት መስሪያ ቤት በተለያየ ሀላፊነት ሲያገለግሉ የነበሩት የአቶ ደገፋው ቦጋለ “ለምን” መፅሀፍ ዛሬ መጋቢት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡
ደራሲው ለስነ ፅሁፍ ባላቸው ዝንባሌ እስከዛሬ ከትበው ያስቀመጧቸውና የህትመት ብርሃን ያላዩ በርካታ መፅሀፎች እንዳላቸው የተገለፀ ሲሆን “ለምን” የተሰኘውና ዛሬ የሚመረቀው መፅሀፋቸው በአባይ ወንዝ ትኩሳት ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው ተብሏል። በምርቃቱ ስነ-ስርአት ላይ ደራሲያን፣ ገጣሚያን ታዋቂ ሰዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች አንደሚታደሙ የተገለፀ ሲሆን፣ በዕለቱ ደራሲና ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ፣ ሊቀ ጠበብት ገብረ ማሪያም ማሞ፣ ገጣሚያኑ ይስሀቅ ግራና  ሀብታሙ ሃይለ ሚካኤል ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ የምርቃቱ አዘጋጅ ሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት አስታውቋል፡፡


Read 1019 times