Sunday, 04 April 2021 00:00

የቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ፍልስፍና 5 እና 6 መፅሐፍት ለንባብ በቁ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

  የእውቁ ጋዜጠኛ፣ ደራሲና ፀሀፊ ተውኔት ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ “ፍልስምና 5” እና “ፍልስምና 6” መፅሀፍት ሰሞኑን ለንባብ በቁ፡፡
 ጋዜጠኛና ደራሲው “በፍልስምና 5” መፅሀፍ በስነ-ልቦና፣ ጋብቻና የአዕምሮ ህክምና ዙሪያ አንቱ የተሰኙ ባለሙያዎችን  ቃለ መጠይቅ አድርጎ ያሰናዳ ሲሆን፣ ባለሙያዎቹም በስነ- ልቦና ምንነት በጋብቻ ሁኔታ፣ በአዕምሮ ህክምና ዙሪያ ያሉ ችግሮችን ከነመንስኤው እና መፍትሔው በግልፅ አስቀምጠዋል።
በዚህ መፅሀፍ እውቁ የዕርቅ ማዕድ አዘጋጅና የፖስትሪቲ መስራች እንዳልክ አሰፋ፣የስነ-ልቦና ባለሙያው ኖህ ውብሸት፣ የፖስትሪቲ መስራችና የስነ ልቦና ባለሙያዋ ወ/ሮ ትዕግስት ዋልተንጉስ፣ እውቁ የአዕምሮ ሀኪም ዶ/ር ዮናስ ባህረ ጥበብን ጨምሮ ሌሎችም ባለሙያዎች ጠቃሚ ማህበረሰባዊ ሀሳቦችን ሰንዝረዋል፡፡
“በፍልስምና 6”መፅሀፍ ሀገር፣ ህዝብና ፖለቲካ የተዳሰሱበት ሲሆን እውቅ ፖለቲከኞች እንዲሁ በርዕሰ ጉዳዮቹ ዙሪያ ይሆናል ይበጃል ያሉትን ሀሳብ በሀገር፣ በህዝብና በፖለቲካ ጉዳይ ሰንዝረዋል።
ከእነዚህም መካከል የአብኑ ሊቀ መንበር በለጠ ሞላ፣ የኢዜማው ሊቀ መንበር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ የኦነግ መስራች ሌንጮ ለታና ሌሎችም ተካተውበታል፡፡
“ፍልስምና 5” በ240 ገፅ ተቀንብቦ በ180 ብር ለገበያ ሲቀርብ “ፍልስምና 6” ደግሞ በ275 ገፅ ተመጥኖ በ200 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን “እነሆ” መፅሀፍት መደብር በዋናነት ያከፋፍለዋል፡፡



Read 21220 times Last modified on Saturday, 03 April 2021 19:37