Saturday, 03 April 2021 18:47

ማዕበል የፈጠረው አንድነት

Written by 
Rate this item
(4 votes)

 ከዕለታት አንድ ቀን አንድ የጀልባዎች እሽቅድድም ተካሂዶ ነበር፡፡ ውድድሩ በጀልባዎች የባንዲራ ቀለም ነበር፡፡ በሰባት ቀለማት ተሰይመው ነበር የሚወዳደሩት፡፡
ውድድሩ ተቀለጣጠፈ!
እየተወዳደሩ እየተሸቀዳደሙ - ቀይ ሰማያዊ አረንጓዴ ብርቱካንማ ፣ቡናማ፣ ጉራማይሌ፣ ወይናማ ቀለማት ባንዲራ ይዘው ይሯሯጡ ጀመረ፡፡
በመካከል ከባድ ማዕበል ይነሳል፡፡ ማዕበሉም ጀልባዎቹን ገለባበጣቸው፡፡ ባንዲራ ከባንዲራ ተደበላለቁ፡፡ የት የት እንዳለ አልታወቀም፡፡ ማዕበሉም አላርፍ አለ!
እንዲህ ባንዲራዎቻችን  ተዋህደው አንድ ሲሆኑ ልቦቻችን አንድ ሊሆኑ ያልቻሉበትን ምክንያት ማጣራት መልካም ነው!
አንድነታችን አይቀሬ ነው፤ የምናሸንፈው ለዚሁና ለዚሁ ብቻ ነው! ማዕበል የፈጠረው አንድነት ይሄው ነው፡፡
አንድነታችንን ከፍቅር እንውለደው፡፡ የይስሙላ አንድነት የትም አያደርሰንም፡፡ በእርግብ ላባ፤ በአበባ አልጋ ተኝተን የምናፈራው ምቾትና ህይወት የለም፡፡
ምሁራን ይወያዩ ይግባቡ፤ ቀና ቀናውን ይዩ! አንዘናጋ፡፡ አንዶለል መሰረት ያለው ህይወት ጥርጥር የለውም፡፡ በጥንት ጊዜ የነበረ የግድግዳ ላይ ፅሁፍ፤
“ፅድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም፣
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም
ይለናል፡፡
ደግ ነገር የመስራት ዝግጁነት አገርን ከክፋት ከማዳን አንድ ነው። ይሄ ደግሞ ወጣቱን ከማስተባበር፣ ሴቶችን ከማገዝ፣ አረጋውያኑን ከሟቋቋምና ምሁራኑን ከማጠናከር ጋር የተያዘ ነው፡፡ ስለዚህ ሚዲያው፣ ት/ቤቶች፣ የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በዚህ መልኩ እጅ ለእጅ መያያዝ አለባቸው!
ማዕበል የፈጠረው አንድነት የምንለው ይሄንኑ ነው!!


Read 11556 times