Saturday, 17 April 2021 11:36

የኮሮና ፅኑ ታማሚዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን አሻቅቧል

Written by  መታሰቢያ ሳሣዬ
Rate this item
(1 Vote)

 በሳምንቱ 12 ሺ 864 አዲስ ታማሚዎችና 194 በበሽታው ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ተመዝግቧል፡፡
ያሳለፍነው ሳምንት በኮሮና ወረርሽኝ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን ያሻቀበበትና የፅኑ ህሙማን ቁጥር በእጅጉ የጨመረበት እንደነበር የጤና ሚኒስቴር መረጃዎች ጠቅመዋል። ከትላንት በስቲያ ሐሙስ ብቻ ለ8ሺ 878 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ፣ 2ሺ 149 ቫይረሱ ሲገኝባቸው፣ የጽኑ ታማሚዎች ቁጥር ወረርሽኙ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ 1031 መድረሱ ታውቋል። በዚሁ ዕለትም 33 ሰዎች በበሽታው መሞታቸውን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡
ባሳለፍነው ሳመንት ውስጥ ብቻ 12ሺ 864 አዳዲስ የኮቪድ ታማሚዎች የተገኙ ሲሆን 194 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሳቢያ ሕይወታቸውን ማጣታቸውን መረጃው ጠቁሟል፡፡


Read 10835 times