Saturday, 08 May 2021 12:44

የታደለች ሀይለ ሚካኤል “ዳኛው ማነው” መፅሐፍ ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በኢህአፓዋ እውቅ ታጋይና ፀሀፊ ታደለች ሀይለ ሚካኤል የተፃፈው፣ በእውቁና ታላቁ ታጋይ ብርሃነ መስቀል ረዳና በራሷ የኢህአፓ ትግልና ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው “ዳኛው ማነው” መፅሀፍ ትላንት ሚያዚያ 29 ቀን 2013 ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በጊዮን ሆቴል ውስጥ በሚገኘው ግሮቭ ጋርደን ዎክ ተመረቀ።
በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር)፣ አርቲስትና የህግ ባሙያ አበበ ባልቻ፣ መራሄ ተውኔት መዓዛ ወርቁ፣ ወ/ሮ ዘውዲ አበጋዝና ሃቂ ብርሃነ መስቀል ረዳ ለምረቃው የሚሆኑ ሀሳቦችን ያቀረቡ ሲሆን ስለ “መሬት ላራሹ” የሚያሳይና በንጉሱ ጌታቸው ተደርሶ የተዘጋጀ አጭር ተውኔት ለእይታ ቀርቧል። ከዚህ በተጨማሪም ከመፅሀፉ ፀሀፊ ታደለች ኃ/ሚካኤል ጋርም ውይይት ተደርጓል።

Read 3196 times