Monday, 10 May 2021 00:00

“ከዶክተርነት ደብተራና ወልይነት” መፅሀፍ ሀሙስ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 በመምህርና ተመራማሪ ሰለሞን በላይ ፋሪስ (ዶ/ር) ተፅፎ ለንባብ የበቃው “ከዶክተርነት ደብተራና ወልይነት” መፅሀፍ የፊታችን ሀሙስ ግንቦት 5 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል።
በእለቱ ግጥም፣ ወግ፣ ዲስኩርና ሙዚቃ የሚቀርብ ሲሆን ገጣሚያኑ ሰይፈ ወርቁ፣ ምግባር ሲራጅና ረድኤት አሰፋ የግጥም ስራቸውን ያቀርባሉ ተብሏል። አርክቴክትና ደራሲ ሚካኤል ሽፈራውና ወ/ሮ ዛፉ አብርሃ ወግ የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ላቀው ዮሐንስ፣ ሀጂ ጀማል ገለቶ እና ፍራኦል ተመስገን ለመድረኩ የሚሆን ሙዚቃ እንደሚያቀርቡና ክራር ደርዳሪው ታምራት ንጉሴ መድረኩን በክራር እያዋዛ እንደሚያመሽ የምርቃቱ የመድረክ አጋፋሪ ጋዜጠኛ ሚካኤል ዓለማየሁ (የእናኑ ልጅ) ለአዲስ አድማስ ገልጿል። መፅሀፉ በ186 ገፅ ተቀንብቦ  በ100 ብር ለገበያ ቀርቧል።

Read 9348 times