Print this page
Monday, 17 May 2021 15:47

በ300 ሚ.ብር የተገነባው ቤዝ ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተመርቆ ሥራ ጀመረ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

  ባለቤትነቱ የቤዝ ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቱር ኤንድ ትራቭል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሆነውና 300 ሚ.ብር እንደወጣበት የተነገረለት “ቤዝ ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል” የተሰኘ ባለ  ኮከብ ሆቴል፣ተመርቆ ስራ ጀመረ፡፡
በተለምዶ አትላስ በሚባለው አካባቢ የሚገኘው ሆቴሉ በ500 ካ.ሜ ላይ ያረፈ ሲሆን 40 ደረጃቸውን የጠበቁ የመኝታ ክፍሎች፣ ለትልልቅና ለመለስተኛ ስብሰባ የሚሆኑ አዳራሾች፣ የተሟላ አገልግሎት የሚሰጡ ባርና ሬስቶራንቶች እንዳሉት የተናገሩት የሆቴሉ ሀላፊዎች፤ ለ100 ሰዎች የስራ ዕድል መክፈቱንም ጠቁመዋል፡፡
ቤዝ ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቱር ኤንድ ትራቭል፤ በአስጎብኚነትና በጉዞ ወኪልነት፣ በአስመጪነትና በላኪነት፣በትራንስፖርት ዘርፍ፣ህንፃ በማከራየትና በመሸጥ እንዲሁም በፋብሪካ አገልግሎት ተሰማርቶ የሚገኝ አገር በቀል ድርጅት መሆኑም ታውቋል ኩባንያው በቀጣይ በተለያዩ አካባቢዎች 10 ሪዞርቶችን የመገንባት እቀድ እንዳለውም የሆቴሉ ባለቤት ገልፀዋል፡፡



Read 1862 times
Administrator

Latest from Administrator