Saturday, 29 May 2021 11:27

ኮሚሽኑ በትግራይ የሰብአዊ መብት ጥሰትን ለመመርመር ተጨማሪ በጀት ጠየቀ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

“የሃገሪቱን አቅም ያላገናዘበ ነው” ገንዘብ ሚ/ር
                       
              በትግራይ ክልል ተፈፀመ የተባለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመመርመር ተጨማሪ በጀት  እንደሚያስፈልገው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል።
ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ጋር በትግራይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራ ለማድረግ እየተዘጋጀ የሚገኘው ኢሰመኮ፤ በክልሉ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለመክፈትና መርማሪዎችን ለመቅጠር ተጨማሪ በጀት የጠየቀው።
ኮሚሽኑ ለ2014 የበጀት ዓመት የተመድ የበጀት ጣሪያ 103 ሚሊዮን ብር ቢሆንም አሁን የጠየቀው 211.6 ሚሊዮን ብር መሆኑ ተመልክቷል። ይህም ከተፈቀደው የ108.6 ሚሊዮን ብር ጭማሪ የበጀት  ፍላጎት መኖሩን አመላካች ነው ተብሏል።
የገንዘብ ሚኒስቴር በበኩሉ፤ ኮሚሽኑ የጠየቀው የበጀት ጭማሪ  የሃገሪቱን አቅም ያላገናዘበ ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በአክሱም ከተማ ባከናወነው የመጀመሪያ ዙር ምርመራ፣ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን ሪፖርት ማድረጉ አይዘነጋም።

Read 11461 times