Sunday, 13 June 2021 00:00

ጦቢያ ግጥም በጃዝ የዛሬ ሳምንት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  ጦቢያ ግጥም በጃዝ የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ ምሽት ከ12፡00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ኢንተርኮንትኔታል  ሆቴል በትልቁ አዳራሽ እንደሚካሄድ ተገለፀ፡፡ አዳራሹ የኮቪድን መስፈርት በሟሟላትና የተመልካችን ቁጥር በመጨመር በጥሩ ሁኔታ ምሽቱን ለማካሄድ መመረጡንም አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡
በዚህ ምሽት ዘመናዊ ውዝዋዜ፣ ግጥም፣ አነቃቂ ንግግር፣ የሙዚቃ ድግስና (የፍራሽ አዳሽ) ወግ የሚካሄድ ሲሆን የመግቢያ ዋጋውም 200 ብር ነው ተብሏል፡፡ ትኬቱን ለማግኘት የቡና ባንክ አካውንት ያለው ሰው በሞባይል ባንኪንግ በኮድ 91993 በBunna `merchant code` ትኬቱን መግዛት የሚችል ሲሆን የቡና ባንክ አካውንት የሌለው በአቅራቢያው ከሚገኝ የቡና ባንክ መግዛት እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡


Read 10963 times