Saturday, 19 June 2021 18:24

“ከእቴጌ ዕሌኒ እስከ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ የኢትዮጵያና የአውሮፓ ግንኙነት” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

የሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አዲስ ሥራ የሆነው “ከእቴጌ ዕሌኒ እስከ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ የኢትዮጵያና የአውሮፓ ግንኙነት” የተሰኘ የምርምር ውጤት መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መፅሀፉ፣መታሰቢያነቱ ዲያቆን ዳንኤል ከዘመናዊቱ ኢትዮጵያ መስራቾች አንዱ ላላቸው ለራስ ጎበና  ዳጬ ያደረገ ሲሆን በዋናነትም መንደርደሪያውን በስመ ጥሩ እንግሊዛዊ የታሪክ ሊቅ ኤድዋርድ ጊበን የታሪክ ብያኔ ላይ አድርጎ፣ በታሪክ ሊቃውንትም ሆነ በታሪክ አዋቂዎች እንደ ጥሬ ሀቅ ይታይና ይወሰድ የነበረውን ይህን ብያኔ ትክክል አለመሆኑን በምርመርና በተጨባጭ ማስረጃዎች የሚተነትንበት ነው ተብሏል፡፡ በስድስት አበይት ክፍሎች የተዋቀረው ይህ የታሪክ ድርሳን፣ከአኩስም ዘመን እስከ 14ኛው መቶ ክፍል ዘመን ያለውን ጊዜ እንደመንደርደሪያ አድርጎ ከ15ኛው እስከ 17ኛው መቶ ክ/ዘመን ያለውን የኢትዮጵያና የአውሮፓ ግንኙነት በተለይም በኢትዮጵያና በፖርቹጋል መካከል የነበረውን ግንኙነትና ተያያዥ ጉዳዮችን በስፋት የሚተነተን ነው ተብሏል፡፡ በ523 ገፅ የተመጠነው መፅሐፉ በ600 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡


Read 13574 times