Saturday, 01 September 2012 11:41

ጀግና መቃብር የለውም

Written by  -ደመቀ ወልዴ-
Rate this item
(0 votes)

አገር ከዳር ዳር ሲያለቅስ - ባንድ ቃል እንደመከረ

ሃዘኑም እንደ ልማቱ - ህዝብን አስተባበረ፤

እንደ ድንገት ደራሽ ጐርፍ - ደግሞም እንደ ሃይል መራሽ

እንዲህ ያል’ የመሪ ፍቅር - በታሪክ አልታየም ጭራሽ

ህልም መሰል እውነታ - በቁሜ አየሁኝ ሣልተኛ

ህዝብ በነቂስ ወጥቶ - አምርሮ ሲያዝን ክፉኛ

መሪ ሲያስለቅስ እንጂ - አላየሁ ሲለቀስለት

እንዴት አድርጌ ልመን - ይህንን ዱብ ዕዳ ክስተት

ጐበዝ ተማር ከዚህ ሰው - የአገር መሲህ ነው በእውነቱ

ራሱን አቅልጦ አለፈ - ልክ እንደ ሻማ በእምነቱ፤

አገር ምድሩ አነባ - ማንም አልቀረም ቤቱ

ለህዝብ መኖር ያስከብራል - ጥልቅ ፍቅር ነው ውጤቱ፤

ውሽንፍር ጐርፍ ሳያግደው - ወገን በሲቃ ተውጦ

በመሪው ያደረ ተስፋው - ድንገት እንደ ሰም ቀልጦ

መቼም አይበረክትም - ትውልድ አገርን ገንቢ

ቅርብ አዳሪ ነው አሉ - ወትሮም ሩቅ አሣቢ፣

ቀብሩ ለምን ታወጀ - ጀግና ምን ቀብር አለው

ማረፊያው የህዝቦቹ ልብ - ሃውልቱም ህያው ሥራው ነው፡፡

የአገሬ ኢትዮጵያ ማህፀን - ሚሊዮን ይውለድ የእማማ

ችግር ጉልበቱ ይራድ - መለስ ያንተን ስም ሲሰማ

ድህነት ታሪክ ይሆናል - ብለሃል አንተም ታይቶሃል

በብልፅግና ህዳሴ - ታሪክህ በወርቅ ይፃፋል፡፡

 

 

 

Read 2051 times Last modified on Saturday, 01 September 2012 11:44