Monday, 02 August 2021 20:12

በአለም በየአመቱ 22 ሚሊዮን…. ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ…….

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(3 votes)

  (ውርጃ) ጽንስን ማቋረጥ ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ጥያቄ መመለስ ከጀመረ ብዙ አመታ ትን አስቆጥሮአል፡፡ ወጣቶች በዚህ ድርጊት ሲጎዱ ወይንም እስከ ሕይወት ፍጻሜ መድረሳቸውን በመገናኛ ብዙሀን ስንገልጽ አመታትን አስቆጠርን፡፡ አመታት በተለዋወጡ ቁጥር ችግሩን ያልሰማ ትውልድ እንደሚተካም ሁሉ  ድርጊቱን የሚፈጽሙት ወጣቶች ብቻም ሳይሆኑ የህክምና ባለሙያዎቹም በአዲስ እየተተኩ ወደስራ እንደሚሰማሩ ግልጽ ነው፡፡ በአለም ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ጽንስን ማቋረጥ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ መሆን ይገባዋል ከሚልም ህግና የአፈጻጸም ደንብ ማውጣታቸው የወጣቱን ሕይወት ለማትረፍ ሲባል በተደረገ አለምአቀፍ ስምምነት መሰረት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬም በዚህ ዙሪያ ወጣቶች እንደሚጎዱ በብዙ ሀገራት በተለይም በኢትዮጵያ ሀገራችን የሚመሰከርለት ጎጂ ድርጊት በመሆኑ ዛሬም የህክምና ባለሙያዎች ለአገልግ ሎቱ ምቹነት ስልጠና ይወስዳሉ፡፡
የህክምና ባለሙያዎች በተጠቀሰው ርእሰ ጉዳይ የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ የተመቻቸ አውደ ጥናት ከሐምሌ 2-4 ድረስ በአዳማ ተካሂዶ ነበር፡፡ ሰልጣኞቹ የተውጣጡት በኦሮሚያና በአማራ ክልል ከሚገኙ ሆስፒታሎች ነው፡፡ ስልጠናው የተሰጠው በፓካርድ ፋውንዴሽን እና በኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ትብብር በሚሰራ ፕሮጀክት አማካኝነት ነው፡፡
ለመሆኑ ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ፤ ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ፤ ህጋዊነትና ህገወጥነት እንዴት ይገለጻል ለሚለው ለዚህ እትም የጋበዝናቸው ዶ/ር ፈሪድ አባስ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት እና በቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትና የስነተዋልዶ ጤና sub- specialist ናቸው፡፡
ዶ/ር ፈሪድ እንዳሉት ውርጃ ወይንም ጽንስ ማቋረጥ በብዙ መንገዶች ሊከፋፈል ይችላል፡፡
ጽንሱ የተቋረጠው በራሱ ሁኔታ ነው ?ወይንስ
ጽንሱ እንዲቋረጥ በተደረገ እርዳታ ነው ? የሚለው በሁለት ተከፍል የሚታይ ነው፡፡
ጽንስ በራሱ ሲቋረጥ አንዳንድ ጊዜ የአፈጣጠር ችግር ያለበት ሆኖ ሊሆን ይችላል፡፡ እንደዚህ አይነት ችግር ያለባቸው ጽንሶች በመጀመሪያው 12/ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ሊቋረጡ ይችላሉ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ጽንሱ እንዲቋረጥ ተፈልጎ በባለሙያ እርዳት የሚፈጸም ሊሆን ይችላል፡፡ እዚህ ጋ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ደህንነቱ ያልተጠበቀ ተብሎ ይከፈላል፡፡
ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ሲባል በሕክምና ባለሙያ የሚሰጥ አገልግሎት እንደመሆኑ አስቀድሞ የሚታየው የጤና ባለሙያው በዚህ ጉዳይ በቂ ልምድና እውቀት አለው ወይ የሚለው ይሆናል፡፡
ሌላው ጽንስን ለማቋረጥ የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች እና ነባራዊ ሁኔታቸዎች ደህንነታቸ ውን የጠበቁ ናቸው ወይ የሚለው መታወቅ ያለበት ጉዳይ ነው፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን የአገልግሎት መመዘኛዎች የአለም የጤና ድርጅት ባስቀመጠው መስፈርት መሰረት የሚታይ ይሆናል፡፡ መስፈርቱ አንድ የጤና ተቋም ለመስጠት የሚፈልገውን የጤና አገልግሎት ለማከናወን የሚያስችለው አቋም አለው ወይንስ የለውም የሚለውን ይመለከታል፡፡
የጤና ተቋሙ መቶ በመቶ እንኩዋን ባይሆን በተቻለ መጠን አቅሙን ያጎለበተ መሆኑ እና አገልግሎቱን የሚሰጠው የጤና ባለሙያ እውቀቱ የተሟላ ከሆነ ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስ የማቋረጥ አገልግሎትን መስጠት ይቻላል ማለት ነው፡፡
ዶ/ር ፈሪድ እንደገለጹት ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ሲባል
እውቀቱ በሌላቸው ወይም ባለሙያ ባልሆኑ ሰዎች ጽንስ ማቋረጥ አገልግሎት ሲሰጥ
በጤና ተቋም ባልተደገፈ ሁኔታ የጽንስ ማቋረጥ አገልግሎት ሲሰጥ ነው፡፡
ባለሙያ ባልሆኑ እና ከጤና ተቋማት ውጪ የሚሰጠው ደህንነቱ ያልተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ ተያይዘው ለሚመጡ የጤና እና ብሎም የሞት አደጋ ሊያጋልጥ ስለሚችል ሊፈጸም የማይ ገባው ተግባር ነው፡፡
ህጋዊና ህገወጥ የሚለው ጽንስን ከመቋረጥ ጋር ተያይዞ የሚገለጸውን ጽንስን የማቋረጥ ድርጊትን ለመፈጸም ድርጊቱ እንዲፈጸምለት የሚፈልገው ግለሰብም ሆነ ፈጻሚው ባለሙያ ይህንን በሚመለከት በሐገሪቱ የወጣውን ህግ አክብሮአል ወይንስ አላከበረም የሚለውን የሚ መለከት ነው፡፡ የተለያዩ ሀገራት የየራሳቸውን ሕግ ያወጡ ሲሆን በኢትዮጵያም በምን ምክንያት ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ሊካሄድ ይችላል የሚለውን ባገናዘበ መልኩ መፈ ጸም አለመፈጸሙን የሚመለከት ይሆናል፡፡
ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥን ተግባራዊ ለማድረግ የወጣው ሕግ ቅድሚያ ትኩረቱ የእናቶ ችን ሞት ለመቀነስ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት አንዲት ሴት ልትቀበለው በማትችለው መንገድ ወይንም በጤና ምክንያትም ይሁን ከኢኮኖሚ እንዲሁም ከማህበራዊ ሁኔታዎች አንጻር ጽንሱን እንዲቋረጥ እፈልጋለሁ ብትል ከእሱዋ ባለፈ የሌላ ሰው ወይንም የባለቤትዋን ፈቃድ መጠየቅ ሳያስፈልግ የሚፈጸም ነው፡፡ በእርግጥ ባለትዳሮች ተነጋግረውና ተስማምተው ድርጊቱ ቢፈጸም ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ባለቤትዋ ፈቃደኛ ባይሆንና እስዋ ግን ከተለያየ አንጻር የምትገ ልጸው ችግር ኖሮ ጽንሱ እንዲቋረጥ ብትፈልግ ሕጉ መብቱን የሚሰጠው ለእስዋ ስለሆነ ደህ ንነቱ የተጠበቀ ጽንስ የማቋረጥ አገልግሎት ማግኘት ትችላለች፡፡
በአለማችን በየአመቱ ወደ ሀያ ሁለት ሚሊዮን የሚደርስ ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ይሰራል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም በአለም ላይ ወደ 47 ሺህ እናቶች ሕይወታቸውን ያጣሉ፡፡ 98%ሚሆኑት እናቶች የሚጎዱት በታዳጊ ሀገራት በተለይም በአፍሪካ የሚከሰት ነው፡፡ በሰለ ጠኑት ሀገራት የእናቶች ሞት በጣም ትንሽ ነው፡፡ በተለይም ከእርግዝና ማቋረጥ ጋር በተገናኘ የእናቶች ሞት በሰለጠኑት ሀገራት ዜሮ በሚባል ደረጃ ነው፡፡ በአፍሪካ ያለው ሁኔታ መለስ ተብሎ ሲታይ የጤና ተቋማቱ ይህንን ችግር ለመቋቋም ዝግጁ ስላልሆኑ እና በደም እጥረት፤የኢንፌክሽን መከላከያ እጥረት በመሳሰሉት  ምክንያቶች ወጣቶቹን ለማዳን የማይቻልበት ሁኔታ በስፋት ይታያል፡፡ ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያንም ጨምሮ የእናቶች ሞት በከፍተኛ ሁኔታ የሚታይበት ነው፡፡
በኢትዮጵያ በጽንስ ማቋረጥ ምክንያት የሚከሰተው ማንኛውንም ጉዳት በተመለከተ ረዥም መስዋእትነት የተከፈለበት ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ እኛ ተማሪ እያለን የነበረው የአገል ግሎት ጥራት እንዲሁም ስንሰማው የነበረው የሞት መጠንና አሁን ካለው ጋር ሲነጻጻር ብዙ እንደተ ሰራበት ይመሰክራል ብለዋል ዶ/ር ፋሪድ፡፡ ጽንስን ማቋረጥ የሚቻለው የእናትየውን ሕይወት ለማዳን ብቻ ነው በሚባልበት ዘመን እና በቅርብ የወጣውና ተግባራዊ የተደረገው ህግ ባልነበረ በት ወቅት ብዙ ሴቶች በአፍላ እድሜያቸው ተቀጭትዋል፡፡ በኢትዮያ 1/3ኛው የእና ቶች ሞት ደህንነቱ ባልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ምክንያት የነበረ ሲሆን አሁን ግን በእጅጉ ቀንሶአል፡፡ በእርግጥ ሙሉ በሙሉ ገና አልተቀረፈም፡፡
ደህንነቱ ባልተጠበቀ መንገድ የሚከናወነው የጽንስ ማቋረጥ መንገዶቹ የተለያዩ ናቸው፡፡ በማህ ጸን ውስጥ በሚገቡ የተለያዩ ነገሮች እንዲሁም በአፍ የሚወሰዱ የመድሀኒቶች ድብልቅ ወይ ንም ባህላዊ የሆኑ አሰራሮች የህክምና እውቀቱ በሌላቸው ሰዎች አማካኝነት ደህንነቱ ባልተ ጠበቀ መሳሪያና ስፍራ የሚካሄድ በመሆኑ የሚፈጠረው ጉዳት በወቅቱም ይሁን እየዋለ እያደረ የሚከሰት በመሆኑ በህክምና ሊረዱ ወደማይችሉበት ደረጃ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ከዚህ ውጤት የሚደርሰው ጉዳት ወይንም ጠባሳ አካላዊ ብቻም ሳይሆን ስነልቡናዊ ጭምር ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ የሚፈጸም ከሆነ የአካልም ሆነ የስነልቡና ችግር ሳይከሰት በሰላማዊ መንገድ ሊጠናቀቅ የሚችል ነው፡፡ ጽንሱን ያቋረጠች ሴትም ምንም አይነት የአካል የስነልቡና ችግር ሳይደርስባት ሕይወትዋን እንድትቀጥልና ወደፊት ባቀደች ጊዜ ልጅዋን የምት ወልድበት እድል እንዲኖራት ያስችላታል፡፡ ነገር ግን በአቅራቢያቸው ከችግሩ የሚያላቅ ቃቸው ባለሙያ ወይንም የጤና ተቋም ባለመኖሩ ምክንያት አገልግሎቱን ለማግኘት ሲሉ የሚሄዱበት መንገድና ገንዘብ ለማግኘት ያደረጉት ጥረት ወይንም መስዋእትነት ተደማምሮ የስነልቡና ጫናውን ሊያበረታው ይችላል፡፡
ወጣቶች፤ተማሪዎች..ወዘተ ከእቅድ ውጪ ወይንም በአስገዳኝ ሁኔታ እና በመሳሰለው መንገድ የተረገዘውን ይሁን በሌላም ምክንያት ጽንስን ለማቋረጥ ሲፈልጉ ምክንያታ ቸውን ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ለሕክምና ባለሙያ አስረድተው አገልግሎት ሊያገኙ እንደ ሚችሉ ሊያውቁ ይባል፡፡            


Read 8490 times