Saturday, 07 August 2021 14:02

ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስ በማቋረጥ…Stigma…መገለል…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)


            ባለፈው ሳምንት እትማችን በአዳማ ጽንስን ደህንነቱ በተጠበቀ ፤ደህንነቱ ባልተጠበቀ፤በህጋዊ፤ሕገወጥ በሆነ መንገድ የሚለውን በመለየት እና የህክምና አገልግሎት ሰጪ የሆኑ የህክምና ባለሙዎች የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት አውደጥናት መካሄዱን አስነብበን ነበር፡፡
በስልጠናው ላይ ከተነሱት አንዳንድ ገጠመኞች የሚከተለው ይገኝበታል፡፡
….ሁለት ሐኪሞች ጉዋደኛሞች ናቸው፡፡ አንዱ ያልተፈለገ ጽንስን ማቋረጥን የሚደግፍ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የማይደግፍ ነው፡፡ በዚህም ብዙ ጊዜ ይጨቃጨቃሉ፡፡ የሚሞቱ እናቶችን ሕይወት ለመታደግ ጽንስን ደህንነቱ በተጠበቀ እና በህጋዊ መንገድ ማቋረጥ ይገባል የሚለውን ሐኪም ሌላኛው ሐኪም ወንጀለኛ ነህ እያለ ይኮንነዋል፡፡ አንድ ወቅት የዚህ ድርጊቱን የማይ ደግፍ ሐኪም የአስራ አምስት አመት እድሜ ያላት ልጅ ሁኔታዋ አላምር ይለዋል፡፡ ነገሩን ሲያረጋግጥም ለካስ እርጉዝ ሆናለች፡፡ ጽንስን ማቋረጥ ትክክል አይደለም ሲል የነበረው ሰው ከሚስቱ ጋር ሲነጋገር ልጅቱ እራስዋን ልትጎዳ እንደምትችል ይገምታል፡፡ ተቃዋቂም ሐኪም አሁን ልጁ እንዳት ሞትበት ይሰጋል፡፡ ስለዚህ ይህንን ያልተፈለገ ጽንስን ማቋረጥ የሚደግ ፈውን ሐኪም ይቅር በለኝ  …ልጄን አትርፍልኝ..ወደፊትም በስራህ አምናለሁ፡፡ ለካስ ሁሉም ተቸግረው ነው ይህን እንዲደረግላቸው የሚፈልጉት ብሎ ይለምነዋል፡፡….   
ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ጽንስን ማቋረጥ የሚቻልባቸው መንገዶች በህግ የተደገፈ አሰራር በአገራችን ቢኖራቸውም አሁንም አንዳንድ ነገሮችን በመሸሽ ደህንነቱ ባልተጠበቀ መንገድ ጽንስን ለማቋረጥ የሚሞክሩ መኖራቸው እሙን ነው፡፡ ጽንስን በማቋረጥ ረገድ ደህንነቱ የተጠበቀውን አሰራር ከሚሸሹት መካከል ከፊሎቹ መገለል ወይንም Stigmaን በመሸሽ መሆኑ በተለያዩ ጥናቶች ታይቶአል፡፡ ይህ መገለል ምንድው ስንል ያነጋገርናቸው ዶ/ር ለሚ በላይ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ኮሌጅ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስትና የቤተሰብ ምጣኔ እና የስነተዋልዶ ጤና subspecialist ናቸው፡፡
መገለል የሚለው ቃል የሚገለጸው አንድ ሰው በሚሰራው ስራ በተለየ አመለካከት በማየት እንዲለይ ወይንም አድልዎ በተመላው መንገድ ምልከታ የሚያደርግበት ስሜት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሩ ስራዎች በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው ተብለው የሚገመቱ ከሆነ ስራውን የሚሰሩ ባለሙያዎችን የተናቀ ወይንም የተጠላ ስራ እንደሰሩ ወይም ስህተት ወይንም ጎጂ ነገርን ጽንስን ማቋረጥ በፈለጉት ላይ እንደፈጸሙ በመገመት መነጋገሪያ እስከማድረግ ይደረሳል፡፡ በዚሁ መንገድም ነገርን በትክክሉ ካለመረዳት የተነሳ ጽንስን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ እንዲቋረጥ በማድረጉ ሂደት እንዲቋረ ጥላቸው ፈልገው ወደጤና ተቋም የሄዱትን ሴቶች ብቻም ሳይሆን ድርጊቱን የሚፈጽሙትን ባለሙያዎች ጭምር አጉል ነገር እንደፈጸሙ በመገመት የማግለል ወይንም የማራቅ ባህርይ ይታያል፡፡ በዚህ ረገድ ጽንሱን በማህጸንዋ በመያዝዋ ከጭንቀት የወደቀችውን ሴት ከማትረፍ ይልቅ ጽንሱን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድም ቢሆን ማቋረጥ ነብስን ማጥፋት በመሆኑ ኃጢአት ነው በሚል አጉል ድምዳሜ ብዙዎች ስህ ተት ይሰራሉ፡፡
ከፕላን ውጪ ወይንም በግድ ተደፍረው ያረገዙ ሴቶች ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ጽንሳቸውን ማቋረጥ ካልቻሉ ቀጣዩ መንገዳቸው የሚሆነው በራሳቸው ላይ በሚወስዱት እርምጃ ሕይወታ ቸውን እስከማጣት የሚያደርሳቸው አስከፊ ገጽታ ሊኖር እንደሚችል በብዛት የሚስተዋል ነው፡፡
የስልጠናው ተሳታፊ የሆኑት የጤና ባለሙያዎቹ ስራውን በሚሰሩበት ወቅት ምን እንደሚሰ ማቸው ተጠይቀው ነበር፡፡ ይህንን ጥያቄ ለሰልጣኞቹ ያቀረቡት ዶ/ር ተስፋዬ ሁሪሳ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ኮሌጅ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስትና የቤተሰብ ምጣኔ እና የስነተዋልዶ ጤና subspecialist ናቸው፡፡ ሰልጣኞቹ ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥን በሚተገብሩበት ጊዜ የሚሰማቸውን ስሜት በተለያዩ ገጽታዎች በማ ድረግ ሃሳባቸውን እንዲገልጹ ነበር የተጠየቁት፡፡ ይህንን ስእል ያቀ ረበው ቢቂላ የሚባል ሲሆን ወደአዳማ ለስል ጠናው የመጣው ከአ ምቦ ሆስፒታል ነው፡፡ ቢቂላ ምርጫው በሆነው ስእል መግለጽ የፈለገው አን ዲት ሴት ባልፈቀደችውና ባላሰበችው መንገድ እርግዝና ሲገጥማት ለራስዋ የምትሰጠው ግምት ተፈላጊ እንዳልሆነችና ከሰው ተራ እንደወጣች አድርጋ ነው፡፡ ከዚህ በሁዋላ እኔ ዋጋ የለኝም ያለችው እና ከሰዎች ተራ የወጣ ችውን ሴት በማጸንዋ የተሸከመችውን ጽንስ ደህንነቱ በተጠ በቀ መንገድ አቋርጦ ወደመደበኛው ሕይወትዋ ማስገባት ያለበት የህክምና ባለ ሙያ ሴትየዋን እራስዋን ከምታሸሽበት ጎትቶ የህክምና አገል ግሎቱን ከሰጠ በሁዋላ ወደሰዎች ተርታ ለማቆም ጥረት ሲያደርግ ያሳያል፡፡
እንደቢቂላ ምስክርነት የህክምና ባለሙያዎችም ቢሆኑ በትክክል ስልጠና ወስ ደው እምነቱ ኖሮ አቸው በፈቃደኝነት ስራውን የሚያከናውኑት ካልሆኑ በስተቀር ትክክል አይደለም ብለው ድር ጊቱን የሚኮንኑ በርካቶች ናቸው፡፡ ቢቂላ በሚሰራበት ሆስፒታል ጽንስ የሚቋረጥበት ክፍል የተለየ ነው፡፡ በሆስፒታሉ ውስጥ ከ18 በላይ አዋላጅ ነርሶችና ወደ መቶ የሚጠጉ ነርሶች ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ጽንስ ከሚቋረጥበት ክፍል ገብተው ስራውን የሚሰሩት አንድ የጽንስና ማህጸን ሐኪም፤ሁለት አዋላጅ ነርሶች እና ሁለት ነርሶች ብቻ ናቸው፡፡ ሌሎቹ ወደክፍሉ እንኩዋን መግባት አይፈል ጉም፡፡ ይህ ስራ ኃጢአት እና ክፉ ስራ ነው ብለው የሚያምኑት ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ሳይሆኑ ከህክምና ባለሙያዎች ውስጥም ናቸው፡፡ አሁን አሁን ተሻሽሎ እና በህግ የተደገፈ ሆኖ እንጂ ቀደም ሲል በነበረው ልምድ ጽንስ ማቋረጥ ነው ከተባለ እንዲያውም ትሂድ፤አንቀ በልም የሚል ምላሽ የሚሰጥበት ወቅት እንደነበረም አይረሳም ብሎአል ቢቂላ፡፡ በቅርብ ጊዜ ባደረግነው ጥናት ላይ ባገኘነው ምላሽ ከአስራ አምስት ሐኪሞች ውስጥ አስራ አራቱ ጽንስን ማቋረጥን የማይደግፉ ሆነው አግኝተናቸዋል ብሎአል ቢቂላ፡፡ ስለዚህም ድርጊቱ ኃጢአት ነው ብለው የሚያምኑ ሰዎች እውነታውን እንዲቀበሉ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ጽንስን ማቋረጥ ደህንነቱ በተጠበቀ እና ህጉ በሚፈቅደው መንገድ ከተከናወነ ሴቶች አለአግባብ የሚያጡት ሕይወት እንዲገታ ያስችላል እንደቢቂላ እምነት፡፡
ዶ/ር ተስፋዬ እንደሚሉት በዚህ ስእል የምንመለከተው ሁለት ነገር ነው፡፡ አንደኛው የህክምና ባለሙያው ከሌሎች የጽንስ ማቋረጥን ድርጊት ከማይደግፉት ባለሙያዎች ተለይቶ ከሰልፉ በመውጣት ሴትየዋን ለመርዳት ሲጎትታት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሴትየዋ ከሌሎች ሰዎች ሰልፍ ውስጥ እራስዋን ለማስገባት ፈቃደኛ ያልሆነች እና ነገር ግን የህክምና ባለሙያው ወደሰልፉ ለማስገባት ሲጎትታት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ በሕክምና ባለሙያዎችም ዘንድ ያለውን መገለል ማስወገድና ሴቶቹም አለአግባብ እንዳይጎዱ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ያሳያል፡፡
ከቀረቡት ስእሎች ውስጥ የተመረጠው ሌላው ስእል የአቢ ድንቁ የሚበራ ሻማ ነው፡፡ ይህ ስእል እንደ አቅራቢው እምነት ሁለት ገጽታ አለው፡፡ በአንዱ ገጽታው ተደፍራም ይሁን ከእቅድ ውጭ እርግዝና የገጠማት ሴት ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ስለሚገባት ጨለማ ውስጥ እንዳለች ትቆጥራለች፡፡ ከገጠማት ጨለማ እራስዋን ለማውጣትም ብዙ ነገር ታስባለች፡፡ ከዚያም መፍትሔውን ስታገኝ ልክ በጨለማ ውስጥ እየበራ ብርሀን እንደሚሰጣት ሻማ ትቆጥረዋለች፡፡ ብርሀን ስታይ ትደሰታለች፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ይህንን ብርሀን እንድታይ የረዳት የህክምና ባለሙያ አለ፡፡ ለህክምና ባለሙያው ደግሞ ባልታቀደ መንገድ ወይንም በግዴታ የተፈጠረን ጽንስ ለማስወገድና የአረገዘችውን ሴት ከችግር ለማላቀቅ ሁሉጊዜ
እንደሚበራ ሻማ እራሱን እያነደደ እንደሻማው እየቀለጠ ብርሀን የሚሰጥ ነው፡፡ የህክምና ባለሙያው ውስን በሆነ ገቢ ሌት ተቀን ቆሞ የተቸገሩትን የሚረዳ ሲሆን እራሴንም በዚህ መንገድ አስቀምጬ ይህን ስእል መረጥኩ ብሎአል አቢ ድንቁ ፡፡
ከዋድላ ወረዳ ሰሜን ወሎ የመጣች ሰልጣኝ ምስክርቷን ስትሰጥ የሚከተለውን ብላለች፡፡
‹‹ ከባለቤቴ ጋር ጽንስን በማቋረጥ ዙሪያ ስንነጋገር እሱ በፍጹም ትክክል አይደለሽም ፡፡ወንጀል …ኃጢአት ነው የምትሰሪው ይለኝ ነበር፡፡ እኔም የተቸገሩትን መርዳት እንዲሁም የሚጠፋ ሕይወትን ማትረፍ ነው እንዴት ይህንን መረዳት ያቅትሀል እለው ነበር፡፡ በሁዋላ ግን አንዴ መለስ በልና ልጃችንን አስባት፡፡ ይቺ ልጃችን እድሜዋ ከፍ ሲል ልታረግዝ ትችላለች፡፡ ይህን መከልከል አትችልም፡፡ እድሜዋ ሳይደርስ…ትምህርቷን ሳትገፋ….አስረግዣለሁ ብሎ ከማያምን ተማሪ አርግዛ ብትገኝ ምን ይደረግ ትላለህ ብዬ ጠየቅሁት፡፡ እሱም አዎን ትክክል ነሽ ብሎ አመነ፡፡ እናም ይህንን ሰዎች እንዲያምኑት ለማድረግ የተቻለው ጥረት መደረግ አለበት ብላለች፡   
በአለማችን በየአመቱ ወደ ሀያ ሁለት ሚሊዮን የሚደርስ ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ይሰራል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም በአለም ላይ ወደ 47 ሺህ እናቶች ሕይወታቸውን ያጣሉ፡፡ 98%ሚሆኑት እናቶች የሚጎዱት በታዳጊ ሀገራት በተለይም ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ነው፡፡


Read 11401 times