Friday, 06 August 2021 00:00

“ኢትዮጵያን መቤዠት” መፅሐፍ ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሶሲዮሎጂ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በሶሻል ሴኩሪቲ አመራር ያገኙትና የጥናትና ፕሮጀክት ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት መስፍን ሀሰን የተፃፈው “ኢትዮጵያን መቤዠት” መፅሐፍ ሀምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሆቴል ተመረቀ።
በማህበራዊ ጥበቃና መምህርነት ለረጅም ዓመታት ባገለገሉት በዚሁ ደራሲ የተፃፈው መፅሐፉ አገራችንን ከገባችበት አጠቃላይ ቀውስና ችግር ለመቤዠት ይሆናሉ ይጠቅማሉ ያሏቸውን በርካታ ሀሳቦች ያስፈሩበት መፅሐፉ በተመረቀበት በዚሁ እለት የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ መሰናዶዎች የቀረቡ ሲሆን፣ አርቲስት ደሳለኝ ሀይሉ፣ ሲሳይ መንግስቴ (ዶ/ር)፣ አርቲስት ሱራፌል ተካ፣ ጋዜጠኛ ዮናስ ክብረት፣ ገጣሚ ፍቃዱ ጌታቸው፣ አዝማሪ ፋሲል ሀአጎስና አርቲስት ፅናት ከበደ ስራቸውን አቅርበዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በፍቃዱ ጌታቸው ተደርሶ በአየሁ ሞላ የተዘጋጀ “እኛው” የተሰኘ አጭር ተውኔት ለእይታ መብቃቱንና መድረኩም በእውቁ ከያኒ ፍቃዱ ከበደ መመራቱን የምርቃቱ አዘጋጅ ፈትል ህትመትና ማስታወቂያ ገልጿል።

Read 823 times