Saturday, 14 August 2021 11:34

የጎዳና ላይ የፋሽን ትርኢት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 በፋብሪክ ዲዛይን ድርጅትና በዲዛይነር ሰናይት ጥበቡ የተዘጋጀውና በሀገራችን መጀመሪያ የሆነው የጎዳና ላይ የፋሽን ትርኢት የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ ነሀሴ 15 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚካሄድ ዲዛይነር ሰናይት ጥበቡ ገለፀች። ጉርድ ሾላ አካባቢ በሚገኘው ግዙፉ ሴንቸሪ ሞል በር ላይ በሚካሄደው በዚህ በዓይነቱ ለየት ያለ የጎዳና ላይ የፋሽን ትርኢት ላይ በአገርኛ ግብአቶች የተሰሩ፣ በአይነታቸው ለየት ያሉና ወቅቱን ያገናዘቡ አልባሳት ለእይታ የሚቀርቡ ሲሆን እነዚህን አልባሳት በማሳየት በኩል የከተማችን ቆነጃጅትና ጎበዛዝት ሞዴሎች እንደሚሳተፉ ዲዛይነርና የፋሽን ትርኢቱ አዘጋጅ ሰናይት ጥበቡ ለአዲስ አድማስ ገልጻለች። በዚሁ የጎዳና ላይ የፋሽን ትርኢት መሰናዶ ላይ የተለያዩ ዲዛይነሮች፣ አልባሳትና  ጨርቃጨርቅ አምራቾች ሞዴሎችና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እንደሚታደሙም ታውቋል።

Read 3147 times