በሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት በየዓመቱ የሚዘጋጀውና አምስተኛ ዙር የሆነው “የአዲስ አመት ተስፋዎቻችን ለሀገራችን” የመፅሐፍት አውደ ርዕይ ረቡዕ ነሀሴ 19 ቀን 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይከፈታል።
እስከ ጳጉሜ 3 ለ14 ቀናት በሚቆየው በዚህ አውደ ርዕይ በርካታ የመፅሐፍት መደብሮች የሚሳተፉ ሲሆን፣ ከገበያ የጠፉና ተፈላጊ መፃህፍት ለሽያጭ እንደሚቀርቡና በሁሉም መፅሐፍት ላይ ከ20-50 በመቶ ቅናሽ እንደሚደረግባቸው የአውደርዕዩ አዘጋጅና የሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ዓለሙ ገልጿል።
በአውደ ርዕዩ ከግለ ታሪክ፣ እስከ ረጅምና አጭር ልቦለዶች፣ የትምህርት አጋዥ መፅሐፍት፣ የስነ-ልቦናና በርካታ አይነት መፅሐፍት በቅናሽ ለሽያጭ የሚቀርቡ ሲሆን ሁሉም አውደ ርዕዩን እንዲጎበኝና የሚፈልገውን መፅሐፍት እንዲገዛ አዘጋጆቹ ጋብዘዋል።
Sunday, 22 August 2021 12:46
“የአዲስ ዓመት ተስፋዎቻችን ለሀገራችን” የመፅሐፍት አውደ ርዕይ ይከፈታል
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና