Saturday, 21 August 2021 00:00

ኒው ጀነሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተማሪዎቹን ዛሬ ያስመርቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

ላለፉት 20 ዓመታት ተማሪዎቹን በተለይም የውጭ ሀገር ዜጎችን በተለያዩ ትምህርቶች አሰልጥኖ በማስመረቅ የሚታወቀው ኒው ጀነሬሽን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ዘንድሮም ለ18ኛ ጊዜ ዛሬ ነሀሴ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በኦሮሞ ባህል ማዕከል ያስመርቃል።
ዩኒቨርስቲ ኮሌጁ በሀገራችን ከሚገኙ አንጋፋ የግል ኮሌጆች አንዱና ቀዳሚው ሲሆን፣ በሁለት ዋና ዋና ነገሮች እንደሚለይም  የዩኒቨርስቲ ኮሌጁ ባለቤትና ፕሬዚዳንት አቶ ማቲዎስ ግችሌ ይናገራሉ። አንደኛው የውጭ አገር ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማርና በስኬት ማስመረቅ መቻሉ ሲሆን ሁለተኛው በአገራችን በግልም ሆነ በመንግስ ዩኒቨርስቲዎች የማይሰጡ ነገር ግን ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ የትምህርት አይነቶችን መስጠት መቻሉ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።
ዩኒቨርስቲ ኮሌጁ እስከ ዛሬ በ3ቱ ካምፓሶቹ ከ20 ሺህ በላይ ተማሪዎችን  አስተምሮ ያስመረቀ ሲሆን፣ ዛሬም በድህረ ምረቃና በቅድመ ምረቃ ያሰለጠናቸውን በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ዜጎች ተማሪዎችን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የተመራቂ ወላጆችና ጥሪ የተደገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት እንደሚያስመርቅ ለማወቅ ተችሏል።


Read 974 times