Print this page
Saturday, 21 August 2021 00:00

“ሐዊር” መፅሐፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ነዋሪነቷን በሲዊዘር ላንድ ያደረገችው ደራሲ ሚሚ ፈቃደ በሲውዘርላንድና በሌሎች ሀገራት የተጓዘችበትንና የጉዞዋን ሁኔታ  የተረከችበትና የጉዞ ማስታወሻዬ ነው ያለችውን “ሐዊር” ከሸገር እስከ ጄኔቫ የተሰኘ እውነተኛ ታሪክ መፅሐፍ ለንባብ ያበቃች ሲሆን ዛሬ ነሐሴ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሆቴል ይመረቃል ተብሏል።
በእለቱ የመፅሐፍ ዳሰሳና የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ስራዎች ይቀርባሉ የተባለ ሲሆን  ደራሲያንና ገጣሚያን ሥራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡና ከመፅሐፉም የተመረጠው የታሪክ ክፍል ለታዳሚ እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል። ሐዊር መፅሐፍ በ340 ገፅ ተቀንብቦ ሲሆን፣ በ200 ብር እና በ25 ዶላር ለገበያ ቀርቧል።


Read 1026 times