Saturday, 08 September 2012 12:38

ለጤና ጉዳይ አስቀድሞ መከላከል እንደ ዋና መርህ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

ለመከላከል ደግሞ ማወቅና መገንዘብ ዋነኛው መንገድ ነው

2005 ዓ/ም የሰላም፣ የጤና ፣የእድገትና የብልጽግና ይሁን!

የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ከተመሰረተ ወደ 21 አመት ይሆነዋል፡፡ በዚህ ዘመን ውስጥ የስራ እንቅስቃሴው ምን ይመስል እንደነበርና በወደፊቱስ የስራ ሂደት ምን ማድረግ ይጠበቅብናል የሚለውን ከማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት ማብራሪያ እነሆ ለአንባቢ ብለናል፡፡ ለኢትዮያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር መመስረት መነሻ ምክንያት የነበረው ከመመስረቱ በፊት የነበረው የእናቶች ጤና ሁኔታ በጣም አሳሳቢ መሆኑና የእናቶች ሞት ቁጥር በጣም ከፍተኛ ስለነበር ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ያሳሰባቸው ኢትዮጵያውያን የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስቶች በየግላቸው ከሚያደርጉት እናቶችን የማዳን ጥረት ባሻገር በጋራ በመሰባሰብ የተ ሻለ ትርጉም ያለው ስራ መስራት እና አስተዋጽኦ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለው በማመናቸው ይህንን ማህበር ሊመሰርቱ በቅተዋል፡፡ ማህበሩ ሲመሰረት ዋነኛ ትኩረቱ የእናቶችንና የጨቅላ ሕጻናትን ደህንነት መጠበቅና የሞት መጠንን መቀነስ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር እንደውጭው አቆጣጠር በ1992 ዓ/ም ሲመሰረት በኢትዮጵያ የእናቶች ሞት መጠን ከአንድ መቶ ሺህ ወላድ እናቶች ከአንድ ሺህ በላይ ነበር፡፡ ሰለዚህ በወቅቱ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ሲቋቋም በአገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት ይገባቸዋል ተብለው ከሚፈረጁ አንዱን ይቀርፋል ከሚል እሳቤ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር አላማና በኢት ዮጵያ የስነተዋልዶ ጤና ሽፋን ከፍ የሚልበትን መንገድ መቀየስና የጨቅላ ሕጻናትን እንዲሁም ሁሉም ሰው ጤናማ የሚሆንበትን ራእይ ይዞ መንቀሳቀስ ነው፡፡ ይህንንም ለማሳካት ማህበሩ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

የህክምና ሙያተኞች በተለይም በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ የሚሰሩ እውቀታቸውን ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበትንና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ በትን ሁኔታዎች ስልጠና በመስጠት እና በመሳሰሉት ማመቻቸት ፣

በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ ስራውን ለመተግበር የሚያስችሉ በፖሊሲ እና በስትራጂ ደረጃ መሰራት ያለባቸውን ነገሮች ከሴክተሩ ባለቤት ከጤና ጥበቃ ሚኒስር ጋር መስራት፣

ህብረተሰቡ በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ ተገቢው ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ ስለችግሮቹ መንስኤ እና መፍትሔ የት እንዴት ሊያገኝ እንደሚችል ጠቋሚ የሆኑ መረጃዎችን የተለያዩ የመገናኛ ብዙሀንን በመጠቀም ማሰራጨት  ...ወዘተ የመሳሰሉትን ስራዎች ይሰራል፡፡

የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ከተቋቋመበት ማለትም ከዛሬ ሀያ አንድ አመት ጀምሮ በነበረው የስራ ሂደት የማህበሩን አቅም ማጎልበት አንዱ ነበር፡፡ ማህበሩን የመሰረ ቱት የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስቶች በመጀመሪያ ስራውን ይሰሩ የነበረው ሙሉ በሙሉ በበጎ ፈቃደኝነት ሲሆን ነገር ግን ስራውን በተጠናከረ መንገድ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችለው አደረጃጀት አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት የተጠናከረ የስራ መዋቅር እና የስራ ቦታ እንዲኖረው ተደርጎአል፡፡ በዚህም ምክንያት በአሁኑ ወቅት ኢሶግ በአዲስ አበባ የራሱ ጽህፈት ቤት እንዲሁም የፕሮጀክት ቢሮ እና አስፈላጊ ሰራተኞች ተሟል ተውለት ስራውን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ መሑሀ/ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር በስነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ አስ ፈላጊ የሆኑ ስትራጂዎችን እና ጋይድላይኖችን መመሪያዎች ከፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስ ር ጋር በመተባበር ሙሉ በሙሉ ኃላፊነትን በመውሰድ ወይንም በማህበሩ አባላት ያለውን ክህሎትና እውቀት አስተዋጽኦ በማድረግ በመቅረጽ ስራ ላይ እንዲውሉ አድርጎአል፡፡ ማህበሩ እንደውጭው ቆጣጠር እስከ 2005 ዓ/ም ድረስ የስነተዋልዶ ጤና ስትራጂ ያልነበረው ሲሆን በመቀረጹም በሽግግር ወቅት ከወጡት ዋና ዋና ፖሊሲዎች እንደ አንዱ የጤና ፖሊሲ የሚቆ ጠር ነው፡፡ ፖሊሲው በእናቶችና በሕጻናት ጤና ዙሪያ ልዩ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን በሽታን በመከላከልና ጤናን በማበልጸግ ላይም ለሚሰሩ የጤና አገልግሎቶች አቅጣጫ ያስይዛል፡፡  ይህ ንን ፖሊሲ መሰረት በማድረግም የስነተዋልዶ ጤና ስትራጂ በሚነደፍበት ወቅት የማህበሩ አባላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያደረጉ ሲሆን እስትራጂው ለሁለተኛ ጊዜ እንደውጭው አቆጣጠር ከ2010 በሁዋላም አንዳንድ መሻሻልና መስተካከል ያለባቸው ነገሮች ተሰርተው እንደገና ለቀጣዮቹ አምስት አመታት ተነድፎአል፡፡

የኢትዮያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበት የተጉዋዘባቸው 21 አመታት ህብረተሰቡ በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ከፍ እንዲያደርግና አገልግሎቱም በአገርም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ በተሻለ ሁኔታ የተመዘገበበት እንዲሁም የእናቶች ጤና ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ መሆኑ ታምኖበት አጽንኦት የተሰጠበት ነው፡፡  በስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት ዙሪያ መሻሻል ከተደረገባቸው መካከል የቤተሰብ እቅድ ዘዴ ተጠቃሽ ሲሆን በኤችአይቪ ዙሪያ ከእናቶችና ከሕጻናት ጋር በተያያዘ የሚሰሩ ስራዎችም በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ የሚደረ ግባቸው ናቸው፡፡

ማህበሩ በስፋት ከሚንቀሳቀስባቸው የጤና ችግሮች መካከል ኤችአይቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለማስቻል በተለይም ከግል የህክምና ተቋማት ጋር የሚሰራው የ ሓልማ ፕሮጀ ክት አንዱ ነው፡፡ የኤችአይቪ ቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ በእርግዝና፣ በወሊድና ከወሊድ በሁዋላ ሊደረግ የሚገባውን ጥንቃቄ እንዲሁም እናቶች ከሕክምና ባለሙያው ጋር ቀርበው ተክክለኛውን አገልግሎት እንዲጠቀሙ ለማስቻል ድግፍ በሚያደርጉ አካላት እገዛ ማህበሩ እንቅስቃሴ የሚያደርግ ሲሆን ለዚህም ክኒንል ጋይድላይን እንዲቀረጽ ተደርጎ አል፡፡ በዚህ ዙሪያ ወደ ሀምሳ በሚደርሱ የጤና ድርጅቶች ለሕክምና ለሚመጡ እናቶች አስፈላጊው አገልግሎት እንዲሰጥ በመደረጉ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ እናቶች ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራር ተዘርግቶአል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በመደፈር ወይንም በወሲብ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ምን አይነት ጥራት ያለው አገልግሎት ማግኘት እንደሚገባቸው የሚያሳይ የስራ መመሪያ ያልነበ ረበትን ክፍተት ለመሙላት አስፈላጊው መረጃ ተሰርቶአል፡፡

ከስነተዋልዶ ጤና ጋር በተያያዘ የተሰሩት የተለያዩ ጋይድላይኖች በፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስር በሚተዳደሩ የጤና ተቋማት ስር የአገልግሎት ደረጃና ጥራትን ለማስጠበቅ በሚያገለግል ሁኔታ ተዘጋጅቶ የቀረበ በመሆኑም በተግባር ላይ ውለዋል፡፡

ከእናቶች ሞት ጋር በከፍተኛ ሁኔታ ቁርኝት ያለው ሌላው የጤና ችግር ከወሊድ በሁዋላ ወይም በወሊድ ወቅት የሚከሰት የደም መፍሰስ ነው፡፡  ይህ የጤና ችግር በአፍሪካ ደረጃ ከ24 እስከ 33 የሚደርስ ሲሆን በአገራችንም ቀላል የማይባል ችግር ነው፡፡ ይህንን ለማስወ ገድ የሚያስችል መመሪያ የተሰራጨ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ መንግስት የጤና አገልግሎቱን ሽፋን ለማዳረስ በተለይም በመከላከልና ጤናን በማበልጸግ ዙሪያ የሚሰሩ ከ32 ሺህ በላይ የሚ ሆኑ የጤና ኤክስንሽን ሰራተኞች ለህብረተሰቡ ተደራሽ በመሆን ቅርብ በመንቀ ሳቀስ ላይ ናቸው፡፡ በማንኛውም ወሊድ ወቅት ሊከሰት የሚችለውን የደም መፍሰስ አደጋ ለመከላከል መከተል የሚገባውን አቅጣጫ የሚያሳይ መመሪያ የኢትዮያ የጽንስና ማህጸን ሐኪ ሞች ማህበር አዘጋጅቶ በፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስር ተቀባይነት በማግኘቱ በአገር አቀፍ ደረጃ ስራ ላይ ከመዋሉም ባሽገር በአገር ውስጥ ቋንቋዎች በትግሪኛ ፣በኦሮሚኛ እና በአማርኛ ተተርጉሞ ለስራ ምቹ በሆነ ሁኔታ ለባለሙያው ቀርቦ በስራ ላይ ውሎአል፡፡

የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ከፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስርና ከተለያዩ የዩኤን ኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር ወደ ሀያ ሁለት የሚደርሱ ሆስፒታሎች ላይ የድንገተኛ የተሟላ የወሊድ አገልግሎት የሚኖርበትን ሁኔታ የማመቻቸት ስራ ሰርቶአል፡፡ በዚህም ፕሮጀክት ከዋና ከተሞች እራቅ ላሉ ቦታዎች ትኩረት የተሰጠ ሲሆን እነርሱም ጋምቤላ ቤንሻን ጉልና ጉምዝ ትግራይ ሽሬ በአማራ ክልል በላሊበላ በአቃስታ በደብረታቦር በፍኖተ ሰላም እንዲ ሁም በኦሮሚያ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች በሚገኙ ሆስፒታሎች ሲሆን በየሆስፒሎቹ ለሁ ለት እና ከዚያም በላይ ለሆኑ ሐኪሞች ስልጠናን እየሰጡ ሙያዊ እገዛ እንዲያደርጉ የማህበሩ አባላት የሆኑ ሐኪሞችን በመላክ ከፍተኛ ስራ ተሰርቶአል፡፡ እነዚህ ሙያተኞች የስራ ጊዜያቸውን ጨርሰው ሲወጡ በየሆስፒታሎቹ የሰለጠኑት ሐኪሞች በማዋለድ ዙሪያ አስፈላጊ የሆኑ አገልግቶችን ስለሚሰጡ የእናቶች ሞት በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል የሚል እምነት አለ፡፡ በእርግዝና ወቅት ከሚከሰት የደም ግፊት ሕመም የተነሳ ለህልፈት የሚዳረጉ እናቶችን ሕይወት ለመታደግ ሲባል ማግኔዥየም ሰልፌት የተሰኘውን መድሀኒት በሀገር ውስጥ እንዲኖር የተደረገውን ጥረት ከማገዛ ባሻገር በዚህ ምክንያት የሚከሰተውን ሞት እስከሀምሳ በመቶ ለመቀ ነስ ጥረት በመደረግ ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ከፌደራል የጤና ጥበቃ ሚኒስርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በመቶ ሰባት በሚደርሱ ሆስፒታ ሎች ውስጥ ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ የጤና ሰራተኞች ሰልጥነው መድሀኒቱን ችግር በሌ ለው ሁኔታ ለተገልጋዮች የሚሰጡበትን ሁኔታ አመቻችቶአል፡፡

ለጤና ጉዳይ አስቀድሞ መከላከል እንደ ዋና መርህ የሚቆጠር ሲሆን ለመከላከል ደግሞ ማወቅና መገንዘብ ዋነኛው መንገድ ነው፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህ በር ህብረተሰቡ በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ አስፈላጊውን ግንዛቤ እንዲጨብጥ ለማድረግ የተለ ያዩ መሰረታዊ የሆኑ መረጃዎችን በኤፍ ኤም አዲስ ሬድዮ ጣቢያና በአዲስ አድማስ ጋዜጣ አማ ካኝነት ለህብረተሰቡ ያቀርባል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሳይንሳዊ ምርምሮችን በህትመት ለአንባቢ የሚያቀርብበት ጆርናል ያለው ሲሆን በዚህ ጆርናል የማህበሩ አባላትም ሆኑ ከማህበሩ አባላት ውጪ የሆኑ ባለሙያዎች በምርምር ያገኙዋቸውን የስነተዋልዶ ጤና ግኝቶችን ለአንባቢ ያቀ ርባሉ፡፡ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር የምእተ አመቱን የልማት ግብ መሰረት በማድረግ በመጪው የስራ ዘመን የእናቶችን እና የጨቅላ ሕጻናትን ጤና በሚመለከት ግቡን ለማሳካት ከመንግስትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር አገራዊ ግዴታውን ለመወጣት ዝግጁ ነው፡፡ 2004 ዓ/ም በርካታ ስራዎች የተሰሩበት አመት የመሆኑን ያህል በኢትዮጵያ አስደን ጋጭ ሁኔታዎች የተከሰቱበት በአገሪቱ ታላላቅ የሆኑ ሰዎች በህልፈት የተለዩበት አመተምህረት በመ ሆኑ ሁኔታው ፈታኝ ነው፡፡ ሆኖም የተነደፉ እቅዶችን ተግባራዊ በማድረግና የተሻለም በመስ ራት መጪው ዘመን የጤና፣ የሰላም ፣የእድገትና የብልጽግና እንዲሆን በመመኘት ውጤት ማስመዝገብን ማህበሩ እቅዱ አርጎ ይጉዋዛል፡፡

 

 

Read 2410 times Last modified on Saturday, 08 September 2012 12:49