Saturday, 04 September 2021 13:17

አይቤክስ ኮሌጅ ተማሪዎቹን ዛሬ ያስመርቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ባለፉት 13 ዓመታት ባከናወነው የመማር ማስተማር ተግባር በተለይም በቱሪዝም፣በሆቴልና በቢዝነስ ዘርፍ የሚስተዋለውን የሰለጠነ ሰው ሃይል ክፍተት በመሙላት አስተዋፅኦ እያደረገ የሚገኘው አይቤክስ ኮሌጅ በዲግሪ፣ በቴክኒክና ሙያ የትምህርት ዘርፍ ከደረጃ 1-4 ያሰለጠናቸውን 400 ያህል ተማሪዎች ዛሬ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ያስመርቃል፡፡
በእለቱ ከቱሪዝም፣ከትምህርት ሚኒስቴርና ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች የክብር እንግዶች ተገኝተው ተማሪዎቹን እንደሚመርቁ የኮሌጁ ዲን አቶ ተስፋዬ አሰፋ ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡ በዘንድሮው ምረቃ በዲግሪ መርሃ ግብር በሆቴል ማጅመንት 100፣ በቴክኒክና ሙያ መርሃ ግብር በፍሮንት ኦፊስ፣ በምግብና መጠጥ በአካውንቲንግና በማርኬቲንግ ዘርፎች 300 በድምሩ 400 ተማሪዎች እንደሚመረቁ ዲኑ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ዘንድሮ በብቃት ከሚመረቁት እነዚህ ታሪዎች መካከል 264ቱ (70 በመቶዎቹ) ሴቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 30 በመቶ ወንዶች መሆናቸውም ታውቋል፡፡ አይቤክስ ኮሌጅ ከተመሰረተ ጊዜ አንስቶ ከ7 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በማስመረቅ የሰለጠነ ሰው ሀይል ክፍተት ያለባቸውን ዘርፎች በመሙላ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በዕለቱ የክብር እንግዶች፣እጩ ተመራቂዎችና የተመራቂ ቤተሰቦች እንደሚታደሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 16665 times