Sunday, 12 September 2021 00:00

September- ስለፕሮስቴት ካንሰር ግንዛቤ የመጨበጫ ወር፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

እንኩዋን ከዘመን ዘመን በሰላም አሸጋገራችሁ፡፡
2014- የሰላም የጤና የእድገትና ብልጽግና እንዲሆን የኢትዮጵያ የጽንስ እና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ይመኛል፡፡
Prostate Cancer Foundation እንዳስነበበው በውጭው አቆጣጠር ሴፕቴምበር የተሰኘው ወር ከፕሮስቴት ካንሰር ጋር በተያያዘ የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ነው፡፡ በዚህ ወር ሰማያዊ ሪቫ ንን በፕሮስቴት ካንሰር ለሚደረገው ምርምር እገዛ ወይንም ድጋፍ ለሚያደርጉ የህብረተሰብ ክፍ ሎች መገለጫ እንደሆነም ድረገጹ አስነብቦአል፡፡ እነዚህ በበጎ ፈቃደኝነት ምርምሩ እንዲደረግ የሚያግዙ ግለሰቦችና አካላት በሕመሙ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን በመመርመር እና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በመጠቆም ወደፊት በአለም ላይ የተሻለ ግንዛቤ ሊያደርጉ ቃል የገቡ በመሆኑ ይህ ወር የፕሮስቴት ካንሰርን በተመለከተ የግንዛቤ ማዳበሪያ ወር እንዲሆን መወሰኑን ፋውን ዴሽኑ ይገልጻል፡፡
Research Square በተሰኘ ገጽ ላይ ስለፕሮስቴት ካንሰርና ተያያዥ ጉዳዮች በኢትዮ ጵያ ምን ያህል ግንዛቤ አለ በሚል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥላዬ ገብሩ፤ ሁሴን መኮንን እና ነጋልኝ ጌታሁን በ2021/አንድ ጥናት ይፋ አድርገዋል፡፡ ወደጥናቱ ከመዝለቃችን በፊት የአለም የጤና ድርጅት ያወጣውን መረጃ ጥቂት እናስነብባችሁ፡፡
የአለም የጤና ድርጅት እ.ኤ.አ Mar 5, 2020 እንዳወጣው መረጃ እ.ኤአ. በ2015 በኢትዮጵያ በፕሮስቴት ካንሰር የሚያዙ አዲስ ህመምተኞች ቁጥር ወደ 2269 የሚገመት ሲሆን እ.ኤ.አ በ2017 አለም አቀፍ ጫና የሚያሳድሩ ሕመሞች የትኞቹ እንደሆኑ ግምት ሲወሰድ ወደ 1851 የሚሆኑ ወንዶች በፕሮስቴት ካንሰር ምክንያት ለህልፈት ተዳርገዋል። ወደ 33.056 የሚሆኑት ደግሞ ጤንነታቸውን እንዲያገኙ በህክምና ይረዱ ነበር፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ፕሮስቴት ካንሰር በወንዶች ላይ ይበልጥ እየተለመደ እና የታማ ሚዎች ቁጥርም በሀገር ደረጃ እያደገ መሆኑን የሚገልጹ መረጃዎች አሉ፡፡ በሀገር ደረ ጃም ፕሮስቴት ካንሰር በተለይም ለወንዶች በ3ኛ ደረጃ የተቀመጠ ገዳይ የካንሰር ሕመም ነው፡፡ ይህንን ህመም በሚመለከት ወንዶች በህይወት ዘመናቸው አኑዋዋራቸውን በማስተካከል፤የካን ሰር ሕመሙን ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት ፤ የመከላከል እርምጃ በመውሰድ ወይንም አስ ቀድሞ ምርመራ በማድረግ ፕሮስቴት ካንሰርን በሚመለከት ያሉበትን ሁኔታ ማወቅን በሚመለ ከት በኢትዮጵያ ጥናት የተደረገው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ነው፡፡ ጥናቱ የተደረገው በአዲስ አበባ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለምርመራ በቀረቡ ወንዶች ላይ ሲሆን ጊዜውም እ.ኤ.አ February 8 - March 8,2021 ድረስ ለአንድ ወር ያህል ነው፡፡ የጥናቱ ዋና አላማም በፕሮ ስቴት ካንሰርና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ለማወቅ ነው፡፡ በጥናቱ ላይ እንዲሳተፉ  የተመረጡት ህመምተኛ ወንዶች ቁጥር 250/ሲሆን 241(96.4%) የሚሆኑት በትክክል ጥናቱ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል፡፡ ከእዚህም ወደ 3/4ኛ የሚሆኑት ለሕክምናው የቀረቡት ከከተማ ነበር፡፡ በጥናቱ እንዲሳተፉ የተደረጉት ወንዶች አማካይ እድሜም ወደ 52 አመት የሚጠጋ ሲሆን ዝቅተኛው 28 ከፍተኛው ደግሞ 97 አመት ነበር፡፡
በጥናቱ የተሳተፉት ወንዶች የህይወት ታሪክን ጥናቱ በመጠኑ የተመለከተ ሲሆን በጥናቱ ከተሳተፉት 241 ወንዶች ውስጥ ወደ 157 የሚሆኑት(65.1%) ጋብቻ የፈጸሙ ሲሆን በትምህርት ሁኔታም 106(44%) የሚሆኑት በኮሌጅ እና ከዚያም በላይ በሆነ ደረጃ የተማሩ ነበሩ፡፡ ወደ 103(42.7%) የሚሆኑት ስራ ያላቸው ሲሆን በጥናቱ ከተሳተፉት ግማሽ ያህሉ 114(47.3%) የሚሆኑት ወርሀዊ ገቢያቸው ከ2251-8900 የኢትዮጵያ ብር ይደርስ ነበር፡፡ በጥናቱ ላይ ከተሳተፉት አብዛኞቹ 141(58.5%) ስለ ፕሮስቴት ካንሰር ከጤና ባለሙያዎች በመቀጠልም ከመገናኛ ብዙሀን መረጃውን እንዳገኙ ገልጸዋል፡፡
ጥናቱን ያደረጉት ባለሙያዎች እንደገለጹት ፕሮስቴት ካንሰርን በሚመለከት ስላለው ግንዛቤ የተለያዩ ሀገራት ህብረተሰባቸውን የተመለከቱባቸው ጥናቶች መነሻ ሆኖአቸዋል፡፡ በዚ ህም መሰረት ሲያነጻጽሩት በኢትዮጵያ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለምርመራ ከመጡት ወንዶች ስለ ፕሮስቴት ካንሰር ያገኙት የግንዛቤ ልክ 45% ሲሆን በንጽጽር በሩዋንዳ የተደረገው ጥናት ውጤት ግን 75% ነበር። ምናልባትም ለናሙና ከተወሰዱ የህመምተኞች ቁጥር መለ ያየት ወይንም የተወሰደው የህመምተኞች ሁኔታ በሩዋንዳ ለሕክምናው በቀጠሮ ላይ ያሉትን ሁሉ ስለጨመረ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ። በሌላም በኩል በቤኒን ከተደረገው የጥናት ውጤት ጋርም ይለያያል ይላል ጥናቱ፡፡ አሁንም የጥናቱ ውጤት መለያየት ለጥናቱ እንዲያግዝ በናሙናነት ከተወሰዱት ሕመምተኞች አንጻር ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ ምንም እንኩዋን ፕሮስቴት ካንሰርን በሚመለከት ያለው ግንዛቤ በቂ ነው ባይባልም ሁኔታው እንደሚያመለ ክተው ሰዎች በተለየ የህመም አይነት ሲያዙ ከጠቅላላው የህብረተሰብ ክፍል እንደሚለዩና ለመረጃውም ቅርብ ለመሆን እንደሚሞክሩ ነው፡፡
ይህ ጥናት ከተለያዩ ሀገራት ያለውን መረጃ ጨምሮ ያገኘው እውነታ ሰዎች አኑዋኑ ዋራቸው በደህና ወርሀዊ ገቢ የታገዘ ከሆነ ስለተለያዩ ሕመሞች አስቀድሞ ግንዛቤ እንዲኖ ራቸው አቅም ይፈጥርላቸዋል፡፡ ለዚህም እንደማሳያ የሚወሰደው በዴንማርክ እና ናሚቢያ በተደረገው ጥናት ስለካንሰር ሕመም ግንዛቤን ለመፍጠር እንዲያመች በዝቅተኛ ደረጃ ለሚኖሩ ሰዎች   በተደረገው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ስለ ፕሮስቴት ካንሰር የተሻሻለ ግንዛቤ እንዲኖር አስችሎአል፡፡ በዝቅተኛ ደረጃ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ባገኙት ድጋፍ ኑሮአቸው በመለ ወጡ ስለጤ ንነታቸው እንዲያስቡ የሚያስችላቸውን እድል ያገኙ ሲሆን ስለህመሙ ምንነት፤ የሚያስከትለውን ጉዳት እና በተወሰነ ጊዜ የጤንነት ምርመራ ለማድረግ እና ስለግል ጤናቸው የበለጠ እንዲያስቡ በመቻላቸው ሕመሙን ከከፋ ደረጃ ሳይደርስ ለማስቆም ጭምር ተጠቅመው በታል፡፡ ሰዎች በድህነት ወይም በዝቅተኛ ደረጃ ለመኖር ሲገደዱ ቅድሚያ የሚሰጡአቸው ብዙ ችግሮች ስላሉባቸው አስቀድመው ስለጤና ሁኔታ ለማሰብ ሁኔታው ላይፈቅድላቸው ይችላል፡፡ ምናልባትም ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ ወደ ጤና ተቋም ለመሄድም ወጪውን ስለሚፈሩ ላይ ደፍሩ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም በዝቅተኛ ደረጃ ከሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ይልቅ ደህና ገቢ ያላ ቸው ስለጤናቸው አስቀድሞ የማሰብ እድልና የተሻለ ግንዛቤ አላቸው፡፡
ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪም በአንድ ሀገር የኢኮኖሚ መሻሻል ካለ የትምህርት እድል ስለሚሰፋ ይህ የትምህርት እድል መስፋት ደግሞ የሰዎች የመማር ፍላጎት እና የጤና አገል ግሎት እንዲያድግ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰዎች ከፍተኛ ገቢ ቢኖራቸ ውም ጎን ለጎን ስለተለያዩ የጤና ሁኔታዎችና ተያያዥ ነገሮች እውቀትን ለመቅሰም ተነሳሽነትን ያዳብርላቸዋል፡፡
ጥናት በተደረገበት ወቅት ለጥናቱ የተጋበዙ ሰዎች ከሰጡት መልስ እንደታየው ከሆነ ስለፕሮስ ቴት ካንሰር አብዛኛ ውን መረጃ ያገኙት ከጤና ባለሙያዎች እና ከጉዋደኛ እንዲሁም ከመገናኛ ብዙሀን ነው፡፡ ነገር ግን ከመገናኛ ብዙሀን መረጃውን አገኘን የሚሉት መልስ ሰጪ ዎች ቁጥር ውስን ስለሆነ መገናኛ ብዙሀኑ ይበልጥ መረጃ ማስተላለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ መገናኛ ብዙሀን መረ ጃውን ሲያስተላልፉ ለመላው ታዳሚ በመሆኑ እና ብዙ ተከታታይን ማግኘት የሚችሉ በመሆኑ ብዙውን የህብረተሰብ ክፍል ግንዛቤውን እንዲያሳድግ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ከጤና ባለሙያ የሚገ ኘው መረጃ ለሕክምና ሲቀርቡ ውስን በሆነ ደረጃ ሲሆን ከጉዋደኛ የሚለውም የስሚ ስሚ እና ግን ዛቤን ለመፍጠር በሚያመች ሁኔታ አይደለም፡፡ ስለሆነም የፕሮስቴት ካንሰርንም ሆነ የሌሎችን ሕመሞች መነሻና የሚያስከትሉትን ጉዳት እንዲሁም መደረግ የሚገባውን ጥንቃቄ በሚመለከት የመገናኛ ብዙሀን በስፋት ማስተማር የሚችሉባቸው መንገዶች ቢኖሩ ጥሩ መሆ ኑን ጥናቱ ይጠቁማል፡፡
የጤና አገልግሎት ባለሙያዎች ህብረተሰብን ስለጤና የማስተማር ኃላፊነታቸው የጎላ በመሆኑ በጤና ተቋማቱ የሚያገኙዋቸውን ታካሚዎች ከማስተማር ባሻገር የመገናኛ ብዙሀንን በመ ጠቀም ትምህርት አዘል መልእክትን ቢያስተላልፉ ‹‹…ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠ ንቀቅ…›› የሚለውን አባባል ተግባራዊ በማድረግ ለህብረተሰቡ ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ ያመ ቻል፡፡ ስለዚህም የተለያዩ ሀገራት ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የመገናኛ ብዙሀን እና የጤና ባለሙያ ዎች ህብረተሰብን በጤናው ጉዳይ አስቀድሞ ግንዛቤ እንዲኖረው የማድረግ አቅም ስላ ላቸው ወደተግባር እንዲ ለወጥ ያስፈልጋል፡፡
ፕሮስቴት ካንሰር በወንዶች ላይ በእድሜ እና በቀጥታ ከቤተሰብ ጋር በተያያዘ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት ነው፡፡ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለህክምና የመጡ ወንዶች ለቀረ በላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ለህ መሙ የነበራቸው ግንዛቤ እጅግ ዝቅተኛ ነበር፡፡ ስለሆነም በፕሮስቴት ካንሰር ሕመም ዙሪያ የህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲጨምር እና በተለይም ወንዶች ሕመሙ ከካንሰር ደረጃ ሳይደርስ ቶሎ ለማስቆም እና ጤንነታቸው ብሎም ህይወታ ቸው እንዳ ይጎዳ ለማድረግ ግንዛቤ መፍጠር ማስተማር ከጤና አገልግሎቱ እንዲሁም ከመገናኛ ብዙ ሀኑ ይጠበቃል ይላል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥላዬ ገብሩ፤ ሁሴን መኮንን እና ነጋልኝ ጌታሁን በ2021 ያቀረቡት ጥናት፡፡

Read 6488 times