Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Monday, 10 September 2012 13:52

“ሰው ጥሩ ሰው ጥሩ፣

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

እንዴት ናችሁሳ!

የ‘ኢቩ አትሞስፌር’ ነገር ነው! አንድ ሁልጊዜ የሚገርመኝ ነገር…መንፈቅና ዘጠኝ ወር ቺስታ ሆነው የቆዩ ወዳጆቻችን የዋዜማ ጊዜ ፈረንካውን ከየት ነው የሚያገኙት! ግራ ገባና! ይቺ የፈረንጅ ጋዜጣና ቴሌቪዥን ሁሉ ‘ዘ ሴክሬቲቭ ኢስት አፍሪካን ኔሽን’ እያለ ሲጠራት የከረማት አገር ውስጥ የአደባበዩ ‘ፀሐይ የሞቀው’ ሁሉ ምስጢር እየሆነ ተቸግረናል፡፡ እናማ…ሊኢቭ ስለ ሰው ስለ ሰው እያለ የሚያስጨፍር ፈረንካ የሚገኝበትን ዘዴ ለነገረን ወሮታ እንከፍላለን፡፡ ያውም ነጋሪ ቢኖር!

የሆነ ነገር ትዝ አለኝማ…በመሀላችን ያለው አለመተማመን ከመብዛቱ የተነሳ ነገ ስማችንን እንኳን “ስሜ ውቃው ዳር እሰከ ዳር ይባላል…” ብለን ለመናገር እያስቸገረን ሳየሄድ አየቀርም፡፡ የምር አሳሳቢ ነገርረ ነው፡፡ አለ አይደል… “ስሜን ብነግረው አዋቂ ቤት ወስዶ ምን እንደሚያስጠመጥምበት አውቃለሁ!” አይነት ‘ሜንታሊቲ’ መሀላቸን ገበቶላችኋል፡፡ አለ አይደል… “በአንድ ቀን ስንት ሰዓታት አሉ?” ተብለን ብንጠየቅ “እኔ እንጃ አላውቀውም…” ልንል የምንችልበት ዘመን እየደረስን ነው፡፡ “በሰዓት አስመስሎ ሀያ አራት ቁጥርን እንድጠራ ለምን ፈለገ?” አይነት ሀሳብ ሊገባን ይችላላ!

እናማ…መሰላቸሁ፣ ሕይወት ሙሉ ለሙሉ ‘ሰስፔንስ ፊልም’ ሊሆን እንደማይችል ማወቁ አሪፍ ነው፡፡

የምናያቸው ነገሮች “ዘጠኝ ቁጥር አውቶብስ በየት አድርጎ ነው የሚሄደው?” ተብሎ የተጠየቀው ሰው መልሱን ከሮበርት ሉድለም መጽሐፍ የባሰ ልብ ሰቀላ ሊያደርገው ይሞክራል፡፡ ሀሳብ አለን…ምስጢር ምን ማለት እንደሆነ በቴሌቪዥን ተከታታይ ‘ዘጋቢ ፊልም’ ይዘጋጅልንና መጀመሪያ ‘ቦሶቻችን’ ካዩ በኋላ ወደ እኛ ይምጣልንማ!

እናላቸሁ…የዓለም ኳስ አፍቃሪ አውርቶ የበቃውን ዜና አንዳንዴ በኤፍ ኤሞቻችን ላይ “በሩኒና በአሰለጣኙ መካከል ተፈጠረ ስለተባለው ችግር ወደኋላ እናሰማቸኋለን፣ ጠብቁን…” አይነት ነገር ሲባል…አለ አይደል…አሪፍ አይደለም፡፡እናማ…ይሄነ ሁሉ ያነሳነው ለረጅም ዘመናት በቺስታነት ከርማቸሁ በኢቭ ላይ “ላንቺም ጠጪ ለእኔም አምጪ!” አይነት ለጋስ የምትሆኑ ሰዎቻችን የፈራንካውን መገኛ ምስጢር ሹክ በሉንማ!

ስሙኝማ…ኽረ ነገርዬው እንዴት ነው፣ ግራ ተጋብተናላ! ‘ሰው’ ጠፋ እንዴ! ልክ ነዋ…መጠየቅ አለብና… የምር እኮ “ዓይኔን ሰው አማረው፣ የሰው ያለህ የሰው” መባል ያለበት ዘንድሮ ነው፡፡

እኔ የምለው…የጣለያን ሱፍ፣ ‘ሲልክ’ ከረባቱ፣ “መሥሪያ ቤታችን ዘንድሮ ባደረገው እንቅስቃሴ…” አይነት ዲስኩሩ…ሁሉም ‘ዝም’ ብሎ ነበር እንዴ! …እንዲሁ ነዋ በየወሩ ሺህ ብር የሚዛቀው! ቂ…ቂ…ቂ… ስሙኝማ…እንግዲህ ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ…በፊት እኮ ሺህ ብር መዛቅ ማለት የባለገንዘበነት ጥግ ማለት ነበር፡፡

“እሷ ምን ታደርግ ትጎርርብን እንጂ፣ ባሏ እንደሁ ሺ ብር ይዝቃል አሉ…” ይባላል፡፡ ይሄኔ አድማጭ ደግሞ ሺህ ብር ብሎ መጀመሪያ አማተቦ ከዛ ራሱን ይይዛል፡፡ ዘንድሮ ግን ሺህ ብር ይዝቃለ ሲባለ የሚያማትብና ራሱነ የሚይዝ ካያችሁ ለሰውየው አዝኖ ነው፡፡ ልክ ነዋ…መቶ ብር ይዞ የአንዲትን ፌስታል ሩብ መሙላት ባስቸገረበት ጊዜ…እንደ ሰሞኑ የእህል ነጋዴዎች ነገር ኩንታል ጤፍ ሁለት ሺህ ብር እየተጠራ “ሺህ ብር ያገኛል…” ማለት ራሱ…አለ አይደል…አንገት የሚያስደፋ አይነት ነገር ነው፡፡

እናላችሁ…ነገሮች ሁሉ ‘ሰው’ ጠፍቶ… “ሰው ጥሩ ሰው ጥሩ፣ ሰው ጥሩ አንድ ሰው…” እያልን ወደምናንጎራጉርበት ዘመነ ላይ ስንደርስ የምር ያሳስባል፡፡ ለስንት ጊዜ ስንት ነገር በቲቪያችን ስናይ ከርመን…አሁን ‘ሰው ሲርበን’ የሆነ የተበላሸ ነገር አለ ማለት ነው፡፡

ስሙኝማ…እንገዲህ ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ… ምን አለ መሰላቸሁ፣ ብዙ ቦታዎች የሚመጥን ‘ሰው’ ስለጠፋ እየተባለ በየወንበሩ ላይ የሚቀመጡት፣ ወይ ተጠባባቂዎች ወይ ተስፈኞች ምናምን ናቸው፡፡ ግርም አይላችሁም…እንዴት ነው በአንድ ዘመን እንዲህ በየዘርፉ፣ በየጓዳው “ዓይናችንን ሰው ሊርበው…” የቻለው!

ስሙኝማ…እግዲህ የበዓል ዋዜማም አይደል…ሀሳብ አለን…የምግብ ማብሰል ባለሙያዎች ምግቦች ሁሉ ያለሽንኩርት የሚሠሩበትን መንገድ ይፈልጉልንማ! አሀ…ከግራና ከቀኝ ተቀባበሉን እኮ! ገና ለገና “በዓል ስለሆነ  የግዳቸውን ይገዟታል” ተብሎ ኪሎ ሽንኩርት ሀያ ብር! ነው…ወይስ ማን ጠያቂ አለን ነው! የምር…ባያሽጓቸውና ነገርየው ባይስተካካል ኖሮ እኮ ጉሮሯችንን አሽገውልን ነበር!

እኔ አንዳንዴ እዚሀ አገር የገበያ እንቅስቃሴ ላይ የሚታየኝ ምን መሰላችሁ…ጭካኔ! ጊዜ እየጠበቁ “ወዶ ሳይሆን በግዱ ይገዛታል…” እየተባለ የሚተመን ተመን ጭካኔ ነው እንጂ የቢዝነስ ስትራቴጂ አይደለም፡፡

ለነገሩም እኛም ሲጎትቱን የምንጎተት የአብረሃም በጎች አይደለን… “አንገዛህም፣ ስትፈልግ ሂድና ጓሮህ ዝራው…” ስለማንል ‘ፒንግ ፖንግ’ ኳስ ሆነን ቀርተናል፡፡

እና መቼም በዓል ጠብቆ የማይመጣብን ነገር የለም…ዘንድሮ ካልጠፋ ነገር በሽንኩርት ጀመረን እላችኋላሁ፡፡

ስሙኝማ…መቼም ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ የሽንኩርትን ነገር ካነሳን አይቀር የሆነች ነገር ትዝ አለችኝማ!…በፊት ስለ አንዷ እንትናዬ ፍሬሽነት በአድናቆት ሲገለፅ “ብታያት እኮ ሽንኩርት ነች!” ምናምን የሚባል አበባል ነበር፡፡

በእርግጥ ትርጉሙ ገብቶኛል ለማለት አልደፍርም፡፡

ቂ…ቂ…ቂ… ግን የሆነ “ሽንኩርት ነች” ሲባል በቃ...አለ አይደል…የሚገልጸው የሆነ ‘ኳሊቲ’ ነገር አለ፡፡

“ለሰበበኛ እንትን መረቅ አታብዛበት” የሚሉት ነገር ነበር፡፡ ዘንድሮ…ልጄ አይደለም መረቅ ማብዛት፣ ሳናሸተው እያንደረደረን ነው፡ ሰበበኞች ሆነናላ! ሰበባችን መአት ነው፡፡ እነንግዲህ በዚሀ በሰባባችን ላይ ነው በዓል፣ ያውም ከስንት ጊዜ አንዴ የረሳነው ፈገግታ ፊታችን ላየ በሚታይበት ጊዜኽ የሆነው አስፈላጊ የሆነ ግብአት ላይ “የግዳቸውን ይገዟታል” እየተባለ ይቆልሉብናል፡፡ እኛም የሄ ልክ አአየደለም፡፡ ለዚህ እጄነ አለሰጥም እነደማለት…“ልጄ ነገ ደግሞ እንደገና ሽቅብ ቢያወጡትስ” ብለን ጭርሱን እንጋፋለን፡፡ ስሙኝማ…እንደው እንዲሀ አይነት ጠባያችንን ጠርጎ የሚያስወግድልን ወይ ስራ ስር ወይ ጠበል ይጥፋ!

ስሙኝማ…እንግዲህ ነገ ያው አዲስ ዓመት አይደል… በስሙ ብቻ ሳይሆን በተግባርም አዲስ ዓመት ያድርግልንማ! ዿግሜ ላይ ሰብስብን እንደምናነጻቸው ልብሶቻችን ልባችንን ሙሉ ለሙሉ የሚያነጻልንን ተአምር አንድዬ ይላክልንማ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሰው እያለ ሰው አጥተን… “ሰው ጥሩ ሰው ጥሩ፣ ሰው ጥሩ አንድ ሰው…” ብሎ ከማንጎራጎር ይሰውረንማ፡፡ እንዲህም ውላችን ጠፍቶ፣ እነዲህም ተዥጎርጉረን፣ እንዲህም ውስጣችን በተለያየ ቶክሲክ ዌስት ተሞልቶ… ተወደደም ተጠላም የምንኖረው ከሰው ጋር ነው፡፡

መልካም በዓል!

ደህና ሰነብቱልኝማ!

 

 

 

 

Read 1492 times Last modified on Monday, 10 September 2012 14:02