Sunday, 03 October 2021 18:41

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የፖለቲካ ጥግ
ነፃነት በማንኛውም ሁኔታ እውን የሚሆነው ሳያሰልሱ በመታገል ብቻ ነው፡፡
አልበርት አንስታይን
ዕድሜ ልክ በባርነት ከመኖር ይልቅ ለነፃት ሲዋደቁ መሞት በስንት ጣዕሙ፡፡
     ቦብ ማርሌይ
እኔን የሚቆጨኝ፤ ለአገሬ የምሰጣት አንድ ህይወት ብቻ ያለኝ በመሆኑ ነው፡፡
ናታን ሃሌ
ዜጎች ሲተባበሩ የማይፈቱት አንዳችም  ችግር የለም፡፡
                   ያልታወቀ ሰው
ጀግኖች የሌላት አገር ጨርሶ ደስተኛ  ልትሆን አትችልም፡፡
                     ቤርትሎት ብረሽት
አገሬ ምን ታደርግልኛለች ሳይሆን ለአገሬ ምን አደርግላታለሁ ብለህ ጠይቅ፡፡
ጆን ኦፍ ኬኔዲ
የማንኛውም አገራት ስኬት፣ መሪዎቻቸው ሌሎችን ለማገልገል ባላቸው ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡     
ጊፍት ሞና
ደስተኝነት ነፃ በመሆን ላይ የተመረኮዘ ነው፤ ነፃነት ደግሞ በደፋርነት ላይ ይመረኮዛል፡፡
ነፃነት፤ ከጥንካሬና ራስን ከመቻል ይመነጫል፡፡
      ሊዛ ሙርኮውስኪ

Read 1043 times