Monday, 18 October 2021 00:00

ዩኒቨርሳል ሜዲካልና ቢዝነስ ኮሌጅ ተማሪዎቹን አስመረቀ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ዩኒቨርሳል ሜዲካልና ቢዝነስ ኮሌጅ ባለፈው ቅዳሜ በኦሮሞ ባህል ማዕከል በተለያዩ ትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸሰውን ተማሪዎች አስመረቀ፡፡
ኮሌጁ ባለፉት 20 ዓመታት በተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች በዲግሪ በዲፕሎማና በሰርተፍኬት መርሃ ግብሮች በርካታ ምሁራንና የጤና ባለሙያዎችን አስመርቆ በሀገሪቱ የልማት እንቅስቃሴ ላይ የራሱን አበርክቶ ያሳረፈ ሲሆን፣ በተለይም በጤናው ዘርፍ የተማረ የሰው ሀይልንን በማሰልጠን በኩል ከፍተኛ ሚና እንደነበረው የኮሌጁ ፕሬዝዳንት በቀለ ምንዳ ባደረጉት ንግግር አስታውሰዋል፡፡
ኮሌጁ ዘንድሮም ለ19ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ሃያ ሁለት ማዞሪያ ካምፓስ በዲግሪ በቴክኒክና ሙያ መርሃ ግብሮች በፋርማሲ፣ነርሲንግ፣እና በህብረተሰብ ጤና የትምገህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ260 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል፡፡ በዕለቱም ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች እጩ ምሩቃንና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ታድመዋል፡፡


Read 10558 times