Sunday, 17 October 2021 00:00

“ኩባ ለአፍሪካ” የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ ለእይታ ይበቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)


            በትውልደ ኢትዮጵያዊ ነጋሽ አብድራህማን የተዘጋጀውና በ32 የዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ላይ በእጩነት የቀረበው “ኩባ በአፍሪካ” (Cuba in Africa) የተሰኘው ዘጋቢ ፊልም ዛሬ ከቀኑ 8፡00  ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአተር ለእይታ ይቀርባል፡፡ የ22 ደቂቃ እርዝማኔ  ያለው ዘጋቢ ፊልሙ በዋናነት ኩባ ለአፈሪካ ነፃነት መቀዳጀት የዋለችውን ከፍተኛ ውለታ የሚያሳይ ነው የተባለ ሲሆን እስካሁን በእጩነት ከቀረበባቸው 32 የፊልም ፌስቲቫሎች የ8ቱ ፌስቲቫሎች አሸናፊ መሆኑ መረጋገጡም ታውቋል፡፡
ዘጋቢ ፊልሙ ኩባውያን ለሰብአዊነት በከፈሉት መስዋዕትነት ለግማሽ ክፍለ ዘመን በአሜሪካ ማዕቀብ ውስጥም ሆነው ሉአላዊትነት እንዳስጠበቁ በክብር የኖሩበትን ፅናት እኛ ኢትዮጵያውያን አሁን በተመሳሳይ ምዕራፍ ላይ ያለን በመሆኑ ከዚህ ፊልም  ብዙ የምንማረው ስለሚኖር ፊልሙ አዲስ አበባ ውስጥ መታየቱ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱም ነው የተገለፀው፡፡ ደራሲው ዘጋቢ ፊልሙን ለማዘጃጀት ኩባ ድረስ መመላለሱ የተገለፀ ሲሆን ለእይታ የሚቀርበው በነፃ ነውም ተብሏል፡፡

Read 10659 times