Saturday, 23 October 2021 14:21

ሕጻናት ለገና አባት የጻፉት ደብዳቤ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ውድ የገና አባት፡-
ለገና ምንም ስጦታ አልፈልግም፤ አንድ ውለታ እንድትውልልኝ ግን እጠይቅሃለሁ። ይኸውም ለኮቪድ-19 መድሃኒት ፈልገህ እንድታመጣልንና ዓለምን እንድትታደግ ነው። በጣም አመሰግናለሁ።
ከፍቅር ጋር -ጆናህ፤ ዕድሜ- 8
ውድ የገና አባት፡
ኢሊያድ ጁኒዬር እባላለሁ። 4 ዓመቴ ነው። በጣም ጎበዝ ነኝ። ለገና ጥቂት አሻንጉሊቶች እንድታመጣልኝ እፈልጋለሁ። አመሰግናለሁ!
ውድ የገና አባት፡-
ለገና ስጦታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ብታመጣልኝ እወዳለሁ፡-
- ውሻ
- ድመት
- ኮምፒውተር
- ጣፋጮች
- ቪዲዮ ጌም
- አዲስ ቢስክሊሌት
ማይክል፤ ዕድሜ- 5
ውድ የገና አባት፡-
ለዘንድሮ ገና ትንሷን ፈረስ ብታመጣልኝ ይሻላል።
ያለበለዚያ ግን መነጋገር ይኖርብናል።
ሳሚ፤ ዕድሜ- 4
ውድ የገና አባት፡-
አይሁድ ነኝ፤ ግን በጣም እወድሃለሁ። ስለዚህ ለገና ስጦታ እንድታመጣልኝ እፈልጋለሁ። የማታውቀኝ ከሆነ ጸጉሬ ጥቁር፣ የዓይኔ ቀለም ቡኒ ነው።
ዴቪድ፤ ዕድሜ- 9
ውድ የገና አባት፡-
ለገና የምፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው። እሱም ሊዮናርዶ ዲካፒርዮን እቤቴ ይዘህልኝ እንድትመጣ ነው፡፡ ምክንያቱም እሱ ተወዳጅ ይመስለኛል፤ እናም ላገኘው እሻለሁ። ይህንን ካደረግህልኝ ባለውለታዬ ነህ። አመሰግናለሁ።
ሻውን ኔይል፤ ዕድሜ- 8
ውድ የገና አባት፡-
ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ልትሰጠኝ ትችላለህ፡፡ በምስጢር እንደምይዘው ቃል እገባልሃለሁ።
1. ዕድሜህ ስንት ነው…?
2. ጊዜን ማቆም ትችላለህ…?
3. ስንት ህይወት ነው ያለህ…?
4. በቀን ስንት ኩኪሶች ትበላለህ…?
5. ብዙ ቋንቋ ተናጋሪ ነህ…?
6. በፍጥነት የምትጓዘው እንዴት ብለህ ነው…?
ለመልሶችህ አመሰግናለሁ። በሚቀጥለው ዓመት ለተጨማሪ ጥያቄዎች ተዘጋጅ።
ስቲቭ-፤ ዕድሜ -6

Read 1226 times