Saturday, 13 November 2021 13:23

“ለምንን ፍለጋ” ትርጉም መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(2 votes)

    በደራሲ ቪክቶር ኢ.ፍራንክል “Man‘s search for Meaning” በሚል ርዕስ የተፃፈውና በተርጓሚ ሀያሲና የስነ ፅሁፍ ባለሞያ ቴዎድሮስ አጥላው “ለምንን ፍለጋ” በሚል ርእስ ወደ አማርኛ የተመለሰው አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መፅሀፉ “የማጎሪያ ቤት ህይወት “፣”ሎጎቴራፒን በእጭሩ”እና አሳዛኝ ተስፈኝነት “የሚሉ ሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ሲሆን የመፅሀፉ ደራሲ ቪክቶር ኢ.ፍራንክል ካለፈበት አሳዛኝ የማጎሪያ ቤት ህይወት ካሳለፈው አሳዛኝ ታሪክና ከነዚህ ሂደቶች ተነስቶ “ለምን”እያለ የሚጠይቅበት ፣የሎጎ ቴራፒን አስተምህሮ ያስተዋወቀበትና በርካታ የህይወት ተሞክሮና ፍልስፍናን የሚያሳይ እንደሆነ ተርጓሚው ቴዎድሮስ አጥላው በመጽሀፉ መግቢያ ላይ አስፍሯል፡፡
የሚኖርለት “ለምን “ያለው ሰው ማንኛውንም “እንዴት ይቋቋማል” የሚለውን የፍሬድሪክ ኒቼን አባባል ለማንፀሪያነት ያስቀመጠው ተርጓሚው በመፅሀፉ ውስጥ በርካታ የራስን ጥንካሬና መከራን የመቋቋም አቅም ልንፈትሽበት እንደምንችል ጠቁሟል በ192 ገፅ የተቀነበበው መፅሀፉ በ200ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 10906 times