Sunday, 14 November 2021 00:00

የኢኮኖሚ መዋዠቅና የስትራቴጂ አቅጣጫዎች በኢትዮጵያ” ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   በእውቁ የምጣኔ ሀብት ባለሞያ በሀሮን ጋንታ የተጻፈውና በሀገራችን የኢኮኖሚ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ የሚያጠነጥነው “የኢኮኖሚ መዋዠቅና የስትራቴጂ አቅጣጫዎች በኢትዮጲያ “መጽሀፍ የፊታችን ሰኞ ህዳር 6 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ጀምሮ በራስ ሆቴል በድምቀት ይመረቃል፡፡
በእለቱ የመጽሀፍ ዳሰሳ ፣ልዩ ልዩ ንግግሮች፣ ሙዚቃ እና ግጥም ለታዳሚ ይቀርባልም ተብሏል፡፡ የመጽሀፉን ዳሰሳ ገዛኸኝ ፀጋው(ዶ/ር) የሚያቀርቡ ሲሆን የፍልስፍና ምሁሩ ዮናስ ዘውዴና ዶ/ር ሙሉ ደሜ በመጽሀፉ፣ በአጠቃላይ የኢኮኖሚውና በህብረተሰቡ ላይ በፈጠረው ጫና ዙሪያ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዕለቱ “ሻሎም ለኢትዮጵያ” የሙዚቃ ቡድን ሙዚቃ የሚያቀርቡ ሲሆን ገጣሚያኑ በቃሉ ሙሉና ኤሊያስ ሽታሁን እንዲሁም መምህርት ዕፀገነት ከበደ  ግጥምና ወግ እንደሚያቀርቡም ታውቋል፡፡
መግቢያ በነፃ እንደሆነና ፍላጎት ያለው በምርቃቱ ላይ እንዲታደም የመፅሀፉ ደራሲ ጋብዟል፡፡



Read 20138 times