Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 15 September 2012 13:16

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

ዛሬ እውነት ነው ተብሎ የተጮኸለኸት ሁሉ ነገ እልም ያለ ውሸት ሊሆን ይችላል፡፡

ሌኒ ብሩስ

(የአሜሪካ ተሳላቂ ኮሜዲያን)

የተሳሳቱ ጥያቄዎች መጠየቅህን ከተረዱ ለመልሶቹ ፈፅሞ መጨነቅ የለባቸውም።

ቶማስ ፒንቾን

ህዝብ ያለ እውቀት ነፃ መሆንን ከጠበቀ ከዚህ ቀደም ያልሆነውንና ወደፊትም የማይሆነውን እየተመኘ ነው፡፡ ህዝብ ያለ መረጃ ነፃ ሊሆን አይችልም፡፡ ፕሬሱ ነፃ ሲሆንና ሁሉም ሰው ማንበብ ሲችል ሁሉም ነገር አስተማማኝ ይሆናል፡፡

ቶማስ ጀፈርሰን

ነፃነት በሰዎች ልብና አዕምሮ ውስጥ ከሞተ የትኛውም ህገ መንግስት፣ ፍርድ ቤትና ህግ ከመሞት አያድነውም፡፡

ጆን ፐርኪንስ

ነፃነት ማለት ሃላፊነትን መቀበል ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው አብዛኛው ሰው እንደ ጭራቅ የሚፈራው፡፡

ጆርጅ በርናርድ ሾው

የእኔ ነፃነት ካንተ መልካም ሃሳብ እጅግ የላቀ ነው፡፡

በምፖር ስቲከር

ነፃነት ትርጉም አለው ከተባለ ሰዎች መስማት የማይፈልጉትን የመንገር መብት መፍቀድ አለበት፡፡

ጆርጅ ኦርዌል

ሰላምን ከባርነት ጋር ከሚሰጡኝ ነፃነትን ከእነ አደጋው እመርጣለሁ፡፡

ዣን ዣኩስ ሩሶ

ያስቀየማቸውን ነገር ለማስወገድ ከሚጣደፉ ሰዎች ህዝባችንን መመለስ አለብን፡፡

ያልታወቀ አሜሪካዊ

 

 

 

Read 3624 times Last modified on Saturday, 15 September 2012 13:31

Latest from