Saturday, 20 November 2021 14:36

በግንኙነት ጊዜ ሕመም ሊሰማ ይችላል፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(3 votes)

 Jennifer T. Anger, MD   Oct 01, 2018 Cedars-Sinai Staff በሚለው ድረገጽ ላይ እንዳስነበቡት የወሲብ ግንኙነት ተፈጥሮአዊና በተፈጥሮም አስፈላጊ ነገር ሲሆን በሰላማዊ መንገድ የሚከወን ከሆነ ሕመም የለውም፡፡ በእውነታው አለም ግን ወንዶችም ሆኑ ሴቶች በወሲባዊ ግንኘነት ጊዜ የሚሰማቸው ሕመም ለመኖሩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ወንዶች በወሲብ ጊዜ ሕመም የሚሰማቸው ከሆነ በብልታቸው አካባቢ በሚፈጠር አንዳንድ የጤና ጉድለት ሊሆን እንደሚል መረጃዎች ጠቁማሉ፡፡ ጠባብ ሸለፈት ወይንም በፕሮስቴት እጢ ሕመም ምክንያት እንዲሁም በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት በሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች እና በሽንት ቧንቧ ኢን ፌክሽኖች ምክንያት ወሲብን በመፈጸም ጊዜ ህመም ሊሰማ ይችላል ይላሉ ባለሙያዋ፡፡
በወሲብ ግንኙነት ጊዜ የሚሰማ ሕመምን ከወንዶች ጋር ሲነጻጸር በአብዛኛው በሴቶች ላይ እንደ ሚጎላ በየጤና ተቋማቱ ከሚደረጉ ምርመራዎች መገመት ይቻላል፡፡ ሴቶች በወሲብ ግንኙነት ወቅት የሚሰማቸው ሕመም በእድሜ እና ከዚህ ውጪም በመውለድ እድሜ ያሉትንም ጭምር ሊያሰቃይ እንደሚችል የተለያዩ ጥናቶች ይገልጻሉ፡፡ ለመሆኑ ሴቶች በወሲብ ጊዜ ሕመም ይሰ ማቸዋል ሲባል ምን ማለት ነው ለሚለው መረጃ ያደረግነው ምንጭ የሚከተለውን ይገልጻል፡፡
ሴቶች ወሲባዊ ግንኙነት በሚየደርጉበት ወቅት በብልት እና አካባቢ ወይንም በጀርባ በኩል ከወገብ በታች ባለው ክፍል አካባቢ ግንኙነቱን በማድረግ ላይ እያሉ ወይንም ካደረጉ በሁዋላ ህመም ሊሰማቸው ይችላል፡፡
የወሲብ ግንኙነቱ በሚፈጸምበት ወቅት በከፋ ወይንም ከባድ በሆነ ሁኔታ የሚፈጸም ከሆነ እና በተለይም በመጀመሪያው ግንኙነት ወቅት ሴቶቹ በሚኖራቸው የአካል ጉዳት የተነሳ አለመዳንና ሁልጊዜም ስቃይ እንዲሆን የሚጋብዙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡  
በአሁኑ ወቅት ህመሙ መፍትሔ ሊያገኝ የሚችልባቸው የህክምና መንገዶች አሉ፡፡
Oct 23,2020 ዌብ ሜድ የተሰኘው ድረገጽ እንደሚያክለው በአለም ላይ ይህን ያህል ሴቶች በዚህ ሕመም ይሰቃያሉ ብሎ ለመናገር አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ይህንን ወደህክምና ባለሙያ በመሄድ በግልጽ መናገር የማይችሉ በጣም በርካታ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ያሉ ሲሆን የህመም ምልክቱም የተ ለያየ ስለሆነ ነው፡፡ በቅርብ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ብዙዎች በወሲብ ግንኙነት ጊዜ የተለያየ የሕመም ስሜት ቢኖራቸውም ጥቂቶች ማለትም ከግማሽ በታች የሆኑት ብቻ ወደ ሐኪማቸው በመሄድ ችግራቸውን እንደገለጹ ይታመናል፡፡
በወሲብ ግንኙነት ወቅት የሚከሰት ሕመም ከወገብ በታች በጀርባ አጥንት በልማድ የደም ጋን እየተባለ በሚጠራው ላይ እና በብልት እንዲሁም በአካባቢው ሊሰማ የሚችል ነው፡፡ ህመሙም ቀጣይነት እና ጥልቀት ያለው ወይንም ሊታገሱት የማይችሉት ሕመም ፤ የሚያቃጥል ስሜት ሊሆን ይችላል፡፡  
በወሲብ ግንኙነት ወቅት ሕመም ለምን ይከሰታል?
በወሲብ ግንኙነት ጊዜ ሕመም መሰማት ለእርካታ ማጣት አንድ ምክንያት ነው፡፡ ይህ ሕመም በጊዜው በባለሙያ እርዳታ ካላገኘ በየጊዜው እየተሻለ ከመሄድ ይልቅ እየተባባሰ የሚሄድ ነው፡፡ ለዚህም ችግር እንደመነሻ ምክንያት ሊሆኑ ከሚችሉት ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
የወሲብ ግንኙነት ባህርይ መለወጥ፤
በወሲብ ግንኙነት ምክንያት የሚከሰት ሕመም ድግግሞሽ፤
ስለወሲብ ግንኙነት ባህርይ እና እርካታን ስለማጣት ውይይት ለማድረግ እና መፍትሔውን ለመፈለግ ፈቃደኛ አለመሆን፤
በእድሜ ምክንያት የብልት ግድግዳዎች ደረቅ መሆን፤
ሌሎች ምክንያቶች…ለምሳሌ
የሴቶች ብልት በተለያዩ ምክንያቶች መጎዳት እና መነካት አለመፈለግ፤
ኢንፌክሽን፤
በብልት አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች መኮማተር፤
የሽንት መስመር ኢንፌክሽን እና
በሴቶች የመራቢያ አካል አካባቢ ያለው የቆዳ ሁኔታ(መድረቅ ወይንም አለመ ለጠጥ) በወሲብ ግንኙነት ጊዜ ለሚከሰት ሕመም ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡  
ሴቶች በወሲብ ግንኙነት ወቅት ህመም እንዲሰማቸው በከፍተኛ ሁኔታ ምክንያት ይሆናሉ ከሚ ባሉት ውስጥ የሆርሞን መዛባትም ይገኝበታል፡፡ ሴቶች እድሜአቸው በጨመረ ቁጥር ኢስትሮ ጂን የተባለው ሆርሞን በሰውነት ውስጥ መመረቱን ይቀንሳል፡፡ በዚህም ምክንያት የሴቶች ብልትን የሚያለሰልስ ፈሳሽ እጥረት ከማጋጠሙም በላይ ለወሲብ ግንኙነት ተነሳሽነትን ይቀን ሳል፡፡ በእርግጥ ሆርሞንን የሚተካ ሕክምና ሁኔታውን ሊያሽሽለው እንደሚችል መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡  
ሰዎች አንዳንድ ጊዜ በሚረበሹበት ወይንም በሚጨነቁበት ጊዜ ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ ወደ እርካታ እንደሚወስዳቸው ያምናሉ፡፡ በእርግጥ ለሁሉም ሰው ባይሆንም በፍቅር ጉዋደኛ ወይንም በትዳር አጋር አማካኘነት ከችግሩ ለማላቀቅ በሚደረግላቸው እንክብካቤ መነሻነት ወደ ወሲባ ግንኙነት ለመግባት ዝግጁ ሊሆኑ ይቸላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሙዚቃ ማዳመጥ፤ቪድዮ ወይንም ቴሌቪዥን መከታተል ሰውነትን ዘና ሊያደርግ ይችላል፡፡ በጀርባ አጥንት አካባቢ ያሉትን ጡንቻዎች እንዲዝናኑ ማድረግም አንዱ ስሜ ትን ለመፍጠር ከሚጠቅሙ ዘዴዎች መካከል ነው፡፡
ሴቶች በወሲብ ጊዜ ሊደርስ የሚችለውን ሕመም በሚመለከት እንዳይጨነቁና ስለሁኔታው አስቀድሞ ውኑ እንዲያውቁ ለማድረግ ትምህርት መስጠት ጠቃሚ ነው፡፡ ስለወሲባዊ ግንኙነት ባህርይ እና ተገቢ የሆነ ምላሽን ስለመስጠት ዝግጁነት ካላቸው ጭንቀት እንዳይዛቸው ይከላከልላቸዋል፡፡ የሰውነት አካልን አሰራር ማወቅ፤ወሲባው ድርጊትን መረዳት፤በእድሜ ምክንያት የሚኖሩ ለውጦችን ማወቅ፤በእርግዝና እንዲሁም በወር አበባ መቋረጥ ወቅት የሚኖረውን ልዩነት ማወቅ ስጋትን ይቀንሳል፡፡ ሴቶች በወሲብ ግንኙነት እራሳቸውን ዘና ማድረግ እንዳለባቸው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ሴቶች በወሲብ ግንኙነት ጊዜ የሚሰማቸው ሕመም ከወንድ ጋር በሚገናኙበት ቅጽበት ወይም የወሲብ ግንኙነቱ እንዳበቃ ሊጀምር ይችላል፡፡
ሕመም መኖሩን ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል፡-
ግንኙነት በሚፈጽምበት ወቅት ኃይለኛ ሕመም ወይንም የማቃጠል ስሜት፤
ከግንኙነት በሁዋላም ሆነ በግንኙነት ወቅት የማያቋርጥ ሕመም፤
የጡንቻ መኮማተር፤ከወገብ በታች ሕመም ፤የጡንቻ ዘና ያለማለት የመሳሰሉት ሕመሞች ምልክቶች ናቸው፡፡
በግንኙነት ጊዜ ሕመም አለ ሲባል በሁለት አይነት ሊከፈል እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ እሱም ቀዳሚና ተከታይ በሚል ይለያል፡፡ ይሄ ሲባልም ህመሙ በዘላቂነት መኖርና ጊዜያዊ መሆኑን የሚያ መለክት ነው፡፡
አንዲት ሴት ምንም አካላዊ የጤና ጉድለት ሳይኖርባት በወሲብ ግንኙነት ጊዜ ሕመም ሊሰማት እንደሚችል ይታወቃል፡፡ ይህም ምናልባት ከስነልቡና ጋር የሚያያዝ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡አንዲት ሴት ወሲብ በምትፈጽምበት ጊዜ ለየት ያለ ነገር ከገጠማት ምንጊዜም የህክምና ባለሙያዋን ማማከር ይገባታል፡፡ በግንኙነቱ ወቅት ህመም ወይንም መድማት እና ያልለመ ደችው ወይንም የተለየ ፈሳሽ ካየች ወደሕክምና ለመሄድ ነገ ዛሬ ማለት የለባትም፡፡ ከወሲብ ግንኙነት ጋር በተያያዘ የሚደርስን ሕመም በቅርብ በሚገኝ ጤና ጣቢያ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች፤ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስቶች ወይንም ሌሎች እንደ የስነልቡና እና የስነአእምሮ ሕክምና ባለሙያዎች …ወዘተ የመሳሰሉትን ማማከር ወደትክ ክለኛው ሕክምና ለማምራት የተገባ ይሆናል፡፡ በወሲብ ግንኙነት ጊዜ የሚሰማ ሕመም እንደ ድንገተኛ ሕመም የማይወሰድና በድንገተኛ ሕክም ናን መሻትን ላይጠይቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን አንዲት ሴት የሚከተሉት ሁኔታዎች ካጋጠሙዋት በፍጥነት ወደሕክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋታል ፡፡
ቀደም ሲል ከምታውቀው ሕመም በከፋ ሁኔታ መራራ የሆነ እና ለመሻልም ጊዜ የፈጀ ከሆነ ወደሕክምና መሄድ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡
መድማትና ተከትሎም የከፋ ሕመም ካለው ወደባለሙያ መሄድ ያስፈልጋል፡፡
ሕመም፤ትውከት ወይም በብልት አካባቢ ከፍተኛ ስቃይ ካለ ፤ማቃጠል…ወዘተ የመሳሰሉት ካሉ ሐኪምን ማናገር ያስፈልጋል፡፡
ብዛት ያለው ፈሳሽ ከብልት የሚወጣ ከሆነ በፍጥነት ወደ ሕክምና ባለሙያ በመሄድ ማማከር ይስፈልጋል፡፡

Read 14346 times