Saturday, 20 November 2021 14:50

“እናት ኢትዮጵያ ታሸንፋለች” ስዕል ለጨረታ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

    ለ“እናት አገር ጥሪ” የተጀመረው ዘመቻ 100 ኩንታል ሊሞላ ነው

                    የደረሲ በረከት አንዳርጌ ስራ የሆነው “እናት ኢትዮጵያ ታሸንፋለች” የሚል መልዕክት ያለው ስእል ለጨረታ ቀረበ፡፡ ከጨረታው የሚገኘው ገንዘብ ጋዜጠኞቹ ስመኝ ግዛው፣አዜብ ታምሩ፣የምስራች አጥናፉ ሻለቃ የወይን ሀረግ በቀለና ሮዝ መስቲካ ለጀመሩት “የእናት አገር ጥሪ” የተሰኘ የስንቅ ዝግጅት ይውላል ተብሏል፡፡ 1 ሜትር በ90 ሴንቲ ሜትር የሆነውና አክሬሊክ የሆነው ይሔው ስዕል እስከ ዛሬ ድረስ ጨረታው እንደሚቀጥልና ዛሬ ወደ ግንባር በሚላከው 12 ኩንታል የበሶ እህል ዝግጅት በሚካሄድበት ግዮን ሆቴል ግሮቭ ጋርደን ዎክ እንደሚጠናቀቅ ከጋዜጠኞቹ አንዷ ስመኝ ግዛው ለአዲስ አድማስ ገልፃለች፡፡ “የእናት ሀገር ጥሪ” የተባለው የስንቅ ዝግጅት እንስቃሴ በአምስቱ አንጋፋ ጋዜጠኞች ሲጀመር 100 ኩንታል በሶ አዘጋጅቶ በዱር በገደል ለሚወድቀው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ልዩ ሀይል እና ለፋኖ ሚሊሽያ ለመላክ ሲሆን ዛሬ በግሮቭ ጋርደን ዝግጅቱ የተጠናቀቀ 12 ኩንታል በሶ ወደ ግንባር ይላካል ተብሏል፡፡ “የእናት ሀገር ጥሪ” የስንቅ ዝግጅት በተጀመረ በሁለት ሳምንት ውስጥ ከታሰበው 100 ኩንታከል ውስጥ 80 ኩንታል ያህል መሰብሰብ መቻሉንና ቀሪውን 20 ኩንታል በአጭር ጊዜ ውሰጥ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ ሲሆን ይህንን ከግብ ለማድረስም ሆነ በበሶ ዝግጅቱ ላይ ሁሉም በመሳተፍ እገዛ እንዲያደርግ ጋዜጠኞቹ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Read 21360 times