Saturday, 20 November 2021 15:02

15ኛው አለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ጥበብ ለ12ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ በአእምሮ የኢንተርፕረነርሽፕ ማስፋፊያ አገልግሎቶች አክስዮን ማህበር በራስ አምባ ሆቴል ተከበረ።

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

    የእለቱ የክብር እንግዳ ክቡር ፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ ከጠቅላይ ሚኒስትር  ጽ/ቤት  ተገኝተው  የመክፈቻ ንግግር  አድርገዋል። ለታዳሚዎች  ስራ ፈጣሪነትን የሚያነሳሳ አጅግ ጠቃሚ መልእክት አስተላልፈዋል ።ኢትዮጵያ ለእድገትና ለብልጽግና ጉዞዋ በርካታ ስራ ፈጣሪዎች እንደሚያስፈልጓት ገልጸዋል።
የአእምሮ ኢንተርፕረነርሽፕ ማስፋፊያ አገልግሎቶች  አክሲዮን ማህበር ቦርድ ፕሬዘዳንት  አቶ ጌታቸዉ ቢራቱ ባደረጉት ንግግር፤ ለሀገር እድገት የሰላም መኖር መተኪያ የሌለዉ ሁላችንም የበኩላችን ልናበረክት  እንደሚገባን  ታላቅ አጽንኦት  ሰጥተዋል።
የኩባንያው  ዋና ስራ አስካያጅ፡-
ዶ/ር ወሮታው በዛብህ በበኩላቸው ለአስተማማኝ የሀገር ሰላም እድገትና ብሌጽግና ኢንተርፕረነርሽፕ ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
 በእለቱ  12 ባለሙያዎች ጠቃሚ ትምህርቶችና ልምዶችን ለታዳሚው አጋርተዋል። የሰልጣኞች ምረቃም ተካሂዷል ።


Read 1718 times