(የውጭ እርዳታ)
* የውጭ እርዳታ እንደ ኢንቨስትመንት እንደ ወጭ መቆጠር የለበትም።
-ካይ ግራንገር-
* እርዳታ በሃብታም አገራት ያሉ ድሆች፣ በድሃ አገራት ያሉ ሃብታሞችን mየሚደጉሙበት ሂደት ነው፡፡
-ፒተር ቶማስ ባዩር-
* የውጭ እርዳታ ሌቦች መንግስታትን ይለፍላል፡፡
- ጄምስ ቦቫርድ-
* የውጭ እርዳታን አሻፈረኝ ማለቴ እውነት ነው፡፡ ነገር ግን የግል ውሳኔዬ አይደለም- መላው አገሩ ነው አሻፈረኝ ያለው።
- ኢንድራ ጋንዲ-
* አንድ መሪ መቼ እንደሚለቅ የሚወስኑት የአገሩ ህዝቦች እንጂ የውጭ ሃይሎች አይደሉም።
- ፖል ካጋሜ-
* አሜሪካ የውጭ እርዳታችንን በዓለም ዙሪያ እንዴት እንደምናከፋፍል እንደገና ማሰብ አለባት፡፡
- ቴድ ዩሆ-
* የውጭ እርዳታ፣ አሜሪካ በዓለም ዙሪያ ተፅዕኖዋንና ቁጥጥሯን የምታስጠብቅበት መንገድ ነው።
- ጆን ኦፍ. ኬኔዲ-
* የውጭ እርዳታ አስፈላጊ ነው፡፡ በትክክል ከተተገበረ በዓለም ዙሪያ የአሜሪካን ተፅዕኖ በአዎንታዊ ፣መንገድ ያሰራጫል፡፡
- ማርኮ ሩቢዮ-
* በልማት እሳቤና ትግበራ ላይ አብዮት ያስፈልገናል፡፡ የውጭ እርዳታ፣ የዕዳ ቅነሳ፣ የቤተሰብ ምጣኔ ዕቅድ፣ዲሞክራሲ፣ትምህርትና ነፃ ገበያ አላመጡም፡፡
- ዊሊያም ኢስተርሊ-