Saturday, 04 December 2021 13:17

በኢትዮጵያ የአርበኝነት ታሪክ ላይ የሚያጠነጥን የስዕል አውደ ርዕይ ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በኢትዮጵያ የአርበኝነት ታሪክ ላይ የሚያጠነጥን የስዕል አውደ ርዕይ ከትላንት በስቲያ ህዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም  ከቀኑ 9፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ “አለ የስነ ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት” ውስጥ ተከፈተ፡፡ ስዕሎቹ ከአጼ ቴዎድሮስ የመቅደላ የተጋድሎና የመስዋዕትነት ጊዜ ጀምሮ የአድዋን፣የማይጨውንና የቅርቡን የካራማራ ድል ለማምጣት የተደገውን ተጋድሎና ድል የሚያሳዩ ስለመሆናቸው የት/ቤቱ ዳሬይክተር፣ መምህርና ሰዓሊ አገኘሁ አዳነ ድልሳሁ በመክፈቻው ላይ ገልጸዋል፡፡ በት/ቤቱ የ65 ዓመታት ጉዞዎች ውስጥ በኢትዮጵያና በዓለም  አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና ዝና ያላቸው ሰዓሊያን የሳሏቸው የስዕል ስብስቦችም ለእይታ መቅረባቸውን አቶ አገኘሁ ጨምረው የገለፁ ሲሆን በአጠቃላይ ስዕሎቹ በመካከለኛው የኢትዮጵያ ዘመን የተደረጉ የተጋድሎና የድል አውዶችን ቁልጭ አድርገው እንደሚያሳዩ ነው ለማወቅ ተችሏል፡፡ በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ትልልቅ ሰዓሊያን  ምሁራንና የሥዕል አድናቂዎች የታደሙ ሲሆን  ስዕሎቹ ለቀጣይ አንድ ወር ለእይታ ክፍት ሆነው እንደሚቆዩና ፍላጎት ያለው መጥቶ እንዲጎበኝ የት/ቤቱ ዳሬክተር አቶ አገኘሁ አዳነ ጋብዘዋል፡፡


Read 11427 times