Wednesday, 22 December 2021 00:00

በአለማችን ከ55 ሚ. በላይ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ተነገረ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   በመላው አለም በሚገኙ አገራት በግጭቶች ወይም በተፈጥሮ አደጋዎች አስገዳጅነት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለው በአገር ውስጥ በተረጅነት የሚገኙ ሰዎች ቁጥር ከ55 ሚሊዮን ማለፉን አንድ አለማቀፍ ተቋም ሰሞኑን አስታውቋል።
የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ክትትል ማዕከል የተባለው አለማቀፍ ተቋም ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት እንዳለው፣ በፈረንጆች አመት 2020 ብቻ በመላው አለም 40.5 ሚሊዮን ያህል ሰዎች በእርስ በእርስ ግጭቶችና በተፈጥሮ አደጋዎች ሳቢያ ለአገር ውስጥ ተፈናቃይነት ተዳርገዋል፡፡
በአመቱ በተለይ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራትና በመካከለኛው ምስራቅ በርካታ ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለው ለተረጂነት መዳረጋቸውን የጠቆመው የተቋሙ ሪፖርት፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በአገር ውስጥ ተፈናቃይ የሆኑባት ቀዳሚዋ የአለማችን አገር ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች የተፈናቀሉባት አፍጋኒስታን መሆኗን እና አዘርባጃን፣ ባንግላዴሽ፣ ቤኒንና ቡርኪናፋሶ እንደሚከተሉ አመልክቷል፡፡


Read 6298 times