Saturday, 01 January 2022 00:00

ሰምና ወርቅ 5ኛ ዓመቱን በኪነ-ጥበብ መሰናዶ ይከበራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት “ሀገር በክዋክብት” የተሰኘውን የኪነ-ጥበብ መሰናዶ 5ኛ ዓመት በኪነ ጥበብ ዝግጅት ያከብራል። ዛሬ ከ7፡30 ጀምሮ በብሄራዊ ቴአትር በሚካሄደው የኪነጥበብ ዝግጅት ወግ፣ ዲስኩር፣ ግጥምና ሙዚቃ ለታዳሚ የሚቀርብ ሲሆን፣ ዳኛቸው አሰፋ(ዶ/ር)፣ ዶ/ር ምህረት ደበበ፣ ትንግርቱ ገ/ፃዲቅ (ረ/ፕ)፣ አርቲስት ሱራፌል ተካ፣ ደራሲ ህይወት እምሻው፣ ገጣሚና ደራሲ ኤፍሬም ስዩም፣ የህግ ባለሙያ ከፈለኝ ካሳ፣ ገጣሚ ብሌን ባዩ እንዲሁም ኪሩቤል ግጥምና ዘፈን ከአድዋ ዘመናዊ ባንድ ጋር በማቅረብ መሰናዶውን የተለየ ያደርጉታልም ተብሏል። የመግቢያ ዋጋው 100 ብር ሲሆን ትኬቶቹ  በጃዕፈርና ዮናስ መጽሀፍ መደብሮች እንደሚገኙም ታውቋል።

Read 13533 times