Sunday, 09 January 2022 00:00

በአሜሪካ ሰኞ ዕለት ብቻ 1 ሚሊዮን የኮሮና ተጠቂዎች ተገኙ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በእንግሊዝ፣ ፈረንሳይና አውስትራሊያ ከፍተኛው የተጠቂዎች ቁጥር ተመዝግቧል
ኦሚክሮን የተባለው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በፍጥነት መስፋፋቱን ተከትሎ፣ በአሜሪካ ባለፈው ሰኞ ብቻ ከ1 ሚሊዮን 80 ሺህ በላይ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መገኘታቸው የተዘገበ ሲሆን፣ ይህም ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ በአለማችን የተመዘገበው ከፍተኛው ዕለታዊ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር መሆኑ ተነግሯል።
ማክሰኞ ዕለት ደግሞ በእንግሊዝ 200 ሺህ፣ በአውስትራሊያ 50 ሺህ፣ በፈረንሳይ ከ270 ሺህ በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸውን የጠቆመው ዘገባው፤ ይህም ለአገራቱ ከፍተኛው ቁጥር ሆኖ መመዝገቡን አመልክቷል፡፡
ወረርሽኙ በ3ኛ ዙር ማዕበል እየመታት በምትገኘው ህንድ ርዕሰ መዲና ኒው ዴሊሂ እና  በፋይናንስ ማዕከሏ ግዙፍ ከተማ  ሙምባይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ አዲስ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉ የተነገረ ሲሆን፣ ቻይናም 1.1 ሚሊዮን ህዝብ በሚኖርባት ዩዦው ከተማ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥላለች፡፡
ዜጎቿን ለ4ኛ ዙር ለመከተብ መዘጋጀቷን ከሰሞኑ ይፋ ያደረገችው እስራኤል በበኩሏ፣ ባለፈው ረቡዕ የኦሚክሮን ዝርያ ከፍተኛ ተጠቂዎች ቁጥር ማስመዝገቧን አስታውቃለች፡፡

Read 4825 times