Print this page
Thursday, 13 January 2022 06:02

ሰሜን ኮሪያ የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓ ተነገረ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ደቡብ ኮርያ ለደህንነቴ ያሰጋኛል ስትል፤ ጃፓን ከቁብ አልቆጥረውም ብላለች


ሰሜን ኮሪያ ባለፈው ማክሰኞ በምስራቃዊ የባህር ዳርቻዋ አካባቢ ስኬታማ የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓ መነገሩን የዘገበው ዘጋርዲያን፤ ይህን ተከትሎም ደቡብ ኮርያ ሙከራው ለደህንነቴ ያሰጋኛል ስትል፣ ጃፓን በአንጻሩ ከቁብ አልቆጥረውም ብላ ማጣጣሏን አስነብቧል፡፡
የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የገዢው ፓርቲ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የአገሪቱን ወታደራዊ አቅም የበለጠ ለማሳደግ ቃል መግባታቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ ባለፈው ማክሰኞም በአገሪቱ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ የባለስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፏ መነገሩን አመልክቷል፡፡ የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራው መደረጉን ተከትሎ የደቡብ ኮሪያ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ለመምከር ባካሄደው ስብሰባ፣ የሰሜን ኮሪያው የሚሳኤል ሙከራ ለደቡብ ኮሪያ የደህንነት ስጋት መሆኑን በመግለጽ ድርጊቱን እንዳወገዘው የጠቆመው ዘገባው፤ የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ በበኩላቸው፣ ሰሜን ኮሪያ የፈለገችውን አይነት የሚሳኤል ሙከራ ማድረጓ የራሷ ጉዳይ መሆኑን በመግለጽ ጉዳዩ ለጃፓን ምንም አይነት የደህንነት ስጋት እንደማይፈጥር መናገራቸውን ነው ያመለከተው፡፡ የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሙን ጃ ኢን ከቀናት በፊት ባደረጉት ንግግር፣  ከሰሜን ኮሪያ ጋር ዘላቂ የሰላም ግንኙነት ለመፍጠር ያላቸውን ዝግጁነት ማስታወቃቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ የአገራቱን ግንኙነት መደበኛ ለማድረግ የማይቀለበስ የሠላም አማራጭ ለመከተል እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸውንም ገልጧል።
በተያያዘ ዜና ደግሞ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ የታጠቁት አምስት የጸጥታው ምክር ቤት አባል አገራት የሆኑት አሜሪካ፣ ቻይና፣ ሩሲያ፣ እንግሊዝና ፈረንሳይ በመካከላቸው ከሚታየው የኒውክሌር የጦር መሣሪያ ውድድር ለመታቀብ ቃል መግባታቸውን ባለፈው ሳምንት ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
አገራቱ በኒውክሌር ጦርነት ውድመት እንጂ ድል እንደሌለ በመገንዘብ የኑክሌር የጦር መሳሪያ ፕሮግራሞቻቸውን ላለማስፋፋትና ውድድር ውስጥ ላለመግባት፣ አለመግባባት ሲፈጠርም ችግሮችን ከጦርነት ይልቅ በንግግርና ውይይት ለመፍታት መግባባት ላይ መድረሳቸውን እንዳስታወቁም ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

Read 1218 times
Administrator

Latest from Administrator