Saturday, 15 January 2022 21:43

8ኛው ዓመት “ግጥም በመሰንቆ” የኪነ ጥበብ ምሽት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  የጥምቀት በዓል መዳረሻ ላይ ከሚካሄዱት የበዓል ፌስቲቫሎች አንዱ የሆነው “ግጥም በመሰንቆ” የኪነጥበብ ምሽት ነገ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በጎንደር ቴዎድሮስ አደባባይ በድምቀት ይካሄዳል።
በአትሮኖስ ሚዲያና በጋዜጠኛ ትዕግስት ካሳ የሚዘጋጀው ይሄው የኪነጥበብ ምሽት ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ታሪክ፣ መነባንብና ሌሎች የጥበብ ስራዎች የሚቀርቡበት ሲሆን በዕለቱም ሀኪም አበበች ሽፈራው፣ ድምጻዊ ኤሊያስ ተባባል፣ ድምጻዊት ጠረፍ ካሳሁን (ኪያ)፣ ገጣሚና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሃይለየሱስ፣ ገጣሚና ጋዜጠኛ በረከት በላይነህ፣ የህግ ባለሙያና ገጣሚ ደሱ ፍቅርኤል፣ ጋዜጠኛና ገጣሚ ፍሬህይወት አምባቸው፣ ገጣሚ ፋሲል የእኔአካል፣ ገጣሚ ሙሀመድ አህመድ፣ ገጣሚ ሚስጥረ ወርቁ፣ ገጣሚ ቴዎድሮስ ታከለና ገጣሚ አዳም ተፈራ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡
መድረኩን ጋዜጠኛ ትዕግስት ካሳ እንደምታጋፍረው የኪነ-ጥበብ ምሽቱ አዘጋጆች አትሮኖስ ሚዲያና  ምድረቀደምት ግጥም በመሰንቆ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አስታውቀዋል።


Read 11115 times