በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን ድንበር አሳብረው የገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከትናንት በስቲያ ሃሙስ ድንገተኛ ጥቃት በመክፈት 8 ሰዎችን ሲገድሉ፣ 5ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት በድረ ገፁ አስታውቋል፡፡ በተደጋጋሚ ወቅትና ጊዜ እየጠበቁ ጥቃት የሚሰነዝሩት የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ታጣቂዎች፣ ሃሙስ ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም በኑዌር ዞን አካቦ ወረዳ፣ በካንካን ቀበሌ ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት ነው ጥቃቱን ያደረሱት፡፡ የክልሉ መንግስት ጥቃት አድራሾችን ተከታትሎ ለማደን ጥረት እያደረገ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የተጠናከረ ጥበቃም እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡ ከዚህ ቀደም እነዚሁ ታጣቂዎች በኑዌር ዞና አኙዋ ዞኖች ገብተው በርካታ ህፃናትን አፍነው መውሰዳቸውና ከአንድ መቶ ሰባ በላይ ሰዎችን መግደላቸው ይታወቃል፡፡ በወቅቱ ታፍነው ከተወሰዱ ህፃናት መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑ በተካሄዱ ድርድሮችና በመከላከያ ሃይል ጥረት ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ መደረጉ ይታወሳል፡፡
Created on 23 April 2024
ዘመን ባንክ የሠራተኞቹን ዕውቀትና ክህሎት ለማሳደግ፣ በዓለም ትልቁ የኢንተርኔት የመማሪያ መድረክ ከሆነው ሊንክድኢን ሊርኒንግ ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራረመ፡፡ የዘመን ባንክ የሰው ሀብት ምክትል ዋና ኦፊሰር አቶ ታከለ ዲበኩሉ ስለ ስምምነቱ ሲገልጹ፤ “ዘመን ባንክ ለሰራተኞቹ ቀጣይነት ያለው የመማርና የሙያ እድ
Created on 23 April 2024
(በብርሃኑ በላቸው አሰፋ ፣ የ”ክቡር ልጆች” መጽሐፍ ደራሲ) ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቀን፤ የንባብ ባህልን ለማዳበር፣ ደራስያንንና አታሚዎችን ለማበረታታት ይከበራል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1995 ዓ.ም ነበር ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጽሐፍ ቀን የተከበረው፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህ
Created on 22 April 2024
*በኤክስፖው ከ30ሺ በላይ ለሚሆኑ ጎብኚዎች ነጻ የህክምና ምርመራ ይሰጣልአፍሮ-ኤዥያ ዓለማቀፍ የጤና ኤክስፖ፣ እዚህ አዲስ አበባ በኤግዚቢሽን ማዕከል፣ ከግንቦት 9-11 ቀን 2016 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ፡፡በኤክስፖው ላይ ከ400 በላይ የአገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች፣ ከ30ሺ በላይ ጎብኚዎች
Created on 22 April 2024
በባሮክ ኢቨንት ኦርጋናይዘር አ.ማ የተዘጋጀው የፋሲካ ባዛርና ኤክስፖ ቅዳሜ ሚያዝያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ባለሃብቶችና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ በይፋ ተከፈተ፡፡የፋሲካ ባዛርና ኤክስፖው እስከ ሚያዝያ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋ
Created on 20 April 2024
ብልፅግና “የሚዲያ ሠራዊት” አደረጃጀት የለም ሲል አስተባበለበገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር የሚንቀሳቀሱና ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚል ስያሜ የተሰጣቸው የፓርቲው አባላት፤ መንግሥትን በሚተቹና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ ሐሰተኛ መረጃ የማሰራጨት ዘመቻ ሥርጫትላይ መሳተፋቸውን
• ገዳሙን ለመታደግ ቅዳሜ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ይካሄዳል ገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል የአንድነት ገዳም በ1574
እባክዎ!..አንድ የጎዳና ሰው የበዓል ምሳውን ይሸፍኑልን? እኛ ስማችን ከዚህ በታች የተጠቀሰ ጋዜጠኞችና በጎ አድራጊዎች ሶሻል ሚድያን
ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር ግማሽ ሚሊዮን (500ሺህ) ብር፣ ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ 100ሺ ብር በመስጠት ጀምሯል ደጋግ ኢትዮጵያውያኖች