በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን ድንበር አሳብረው የገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከትናንት በስቲያ ሃሙስ ድንገተኛ ጥቃት በመክፈት 8 ሰዎችን ሲገድሉ፣ 5ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት በድረ ገፁ አስታውቋል፡፡ በተደጋጋሚ ወቅትና ጊዜ እየጠበቁ ጥቃት የሚሰነዝሩት የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ታጣቂዎች፣ ሃሙስ ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም በኑዌር ዞን አካቦ ወረዳ፣ በካንካን ቀበሌ ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት ነው ጥቃቱን ያደረሱት፡፡ የክልሉ መንግስት ጥቃት አድራሾችን ተከታትሎ ለማደን ጥረት እያደረገ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የተጠናከረ ጥበቃም እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡ ከዚህ ቀደም እነዚሁ ታጣቂዎች በኑዌር ዞና አኙዋ ዞኖች ገብተው በርካታ ህፃናትን አፍነው መውሰዳቸውና ከአንድ መቶ ሰባ በላይ ሰዎችን መግደላቸው ይታወቃል፡፡ በወቅቱ ታፍነው ከተወሰዱ ህፃናት መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑ በተካሄዱ ድርድሮችና በመከላከያ ሃይል ጥረት ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ መደረጉ ይታወሳል፡፡

Created on 14 May 2022
• “የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው በኑሮ ውድነቱ ላይ ቤንዚን ማርከፍከፍ ነው” • የነዳጅ እጥረቱ የተከሰተው በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገባው ነዳጅ በኮንትሮባንድ እየተቸበቸበ በመሆኑ ነው • የነዳጅ ድጎማው ሲነሳ የአንድ ሊትር ቤንዚን ዋጋ 66 ብር ከ78 ሳንቲም፤ የአንድ ሊትር ናፍጣ ዋጋ 73 ብር ይደርሳል
Created on 14 May 2022
መንግስት የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመመከት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል የህወኃት ታጣቂ ሃይሎች ለዳግም ወረራና ጦርነት ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸው የተጠቆመ ሲሆን አማፂ ቡድን “የመጨረሻው ምዕራፍ” ላለው ጦርነት የትግራይ ህዝብ እንዲዘጋጅ

Created on 14 May 2022
ከ400 በላይ ኢንዱስትሪዎች ምርት አቁመዋል ተብሏል በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ ከ446 በላይ ኢንዱስትሪዎች በገጠሟቸው የተለያዩ ችግሮች ሳቢያ ምርት አቁመው መዘጋታቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡ለኢንዱስትሪዎቹ መዘጋት በዋናነት የተጠቀሱት ምክንያቶች፡- የጥሬ እቃና የፋይ

Created on 14 May 2022
በመጪው ሰኔ 11 እና 12 ቀን 2014 ዓ.ም አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን የሚያካሂደው ኢዜማ፤ ቀጣይ መሪውን ለየት ባለ የምርጫ ሥርዓት እንደሚመርጥ አስታውቋል፡፡የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ አዋቅሮ ከመጋቢት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ዝግጅቶችን እያከናወነ መሆኑን ያመለከተው ኢዜማ፤ ቀጣይ መሪዎቹን

Created on 14 May 2022
ስልጠናው በመላው አገሪቱ በ20 ከተሞችና በ32 የስልጠና ማዕከላት ለ5 ቀን ተካሂዷል የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ብድር ወስደው ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ ላለፉት 5 ቀናት የዘለቀ ሥልጠና ለ34 ሺ ሰልጣኞች የሰጠ ሲሆን ለእነዚህ ሰ

ዛሬ ምሽት ከ11 ሰዓት ጀምሮ ፤ በአንጋፋው ብሔራዊ ትያትር ሞሰብ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን በልዩ ተሰጥኦና ጥምረት ፣

የዲያስፖራው ደራሲ ዓለማየሁ ማሞ ስራዎች የሆኑት “ከተጓዡ ማስታወሻ” እና “ከአገልጋዩ ማስታወሻ” የተሰኙ የጉዞ ማስታወሻ መፅሐፎች