Saturday, 12 February 2022 12:29

“ሹመትና ቁመት” መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 በደራሲ ጋሻው ሙሉ የተዘጋጀውና “ሹመትና ቁመት” የሚል መጠሪያ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ። መፅሐፉ የተለያዩ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ተያያዥ ጉዳዮችን በተለያዩ ርዕሶች ይዞ የሚሞግት፣ የሚያስተምር፣ የሚያነቃና የሚተች ነውም ተብሏል።
“ሹመትና ቁመት” የተሰኘውን የመጽሐፉን መጠሪያ ጨምሮ 16 ያህል ርዕሶችንና ርዕሰ ጉዳዮችን የያዘው መጽሐፍ በ147 ገፅ ተቀንብቦ በ160 ብርና  በ35 ዶላር ለገበያ ቀርቧል።
ደራሲው ከዚህ ቀደም “እቴ ሙሽራዬ” ተሰኘ የግጥም ስብስብ መፅሐፍ ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም።


Read 29919 times