Sunday, 20 February 2022 17:15

ኤለን መስክ 6 ቢሊዮን ዶላር ለበጎ ምግባር ለገሱ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 የአለማችን የወቅቱ ቁጥር አንድ ባለጸጋ አሜሪካዊው ቢሊየነር ኤለን መስክ፣ ከቴስላ ኩባንያ ውስጥ ካላቸው የአክሲዮን ድርሻ 5.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመተውን ለበጎ ምግባር ስራዎች መለገሳቸው ተነግሯል፡፡
የታዋቂው ኤሌክትሪክ መኪኖች አምራች ኩባንያ ቴስላ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ቢሊየነሩ መስክ፣ በኩባንያቸው ውስጥ ካላቸው ድርሻ 5 ሚሊዮን ያህል አክሲዮኖችን ለበጎ ምግባር መለገሳቸውንና ዋጋውም 6 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ነው ብሉምበርግ የዘገበው፡፡
ቢሊየነሩ ገንዘቡን የለገሱት ለየትኛው የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ለምን አይነት በጎ አድራጎት ስራ እንዲውል እንደሆነ አለመገለጹን የጠቆመው ዘገባው፤ የቢሊየነሩ አጠቃላይ የተጣራ ሃብት 227.3 ቢሊዮን ዶላር መድረሱንም አክሎ ገልጧል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ ኤለን መስክ 6 ቢሊዮን ዶላር ቢሰጠኝ ረሃብን ከምድረገጽ አጠፋለሁ ብሎ በአደባባይ ማስታወቁን ተከትሎ፣ መስክ በበኩሉ #ድርጅቱ በምን መልኩ ረሃብን እንደሚያጠፋው ካረጋገጠልኝ ልሰጠው ዝግጁ ነኝ; ማለቱንም ዘገባው አስታውሷል፡

Read 1617 times