Thursday, 03 March 2022 06:48

የዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ ለ8ኛ ተከታታይ አመት የአለማችን ቁጥር 1 ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ላለፉት 7 ተከታታይ አመታት በአለማችን በርካታ መንገደኞችን በማስተናገድ አቻ ያልተገኘለት የዱባይ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ዘንድሮም 29 ሚሊዮን ያህል አለማቀፍ መንገደኞችን በማስተናገድ የ1ኛነት ክብሩን ማስጠበቁ ተዘግቧል፡፡
የዱባይ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ባለፈው የፈረንጆች አመት ብቻ 29.1 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገዱን የዘገበው ገልፍ ኒውስ፤ ከ2020 ጋር ሲነጻጸር የ12 በመቶ ብልጫ እንዳለውና በተያዘው አመት ደግሞ 55.1 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተናግዳል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁሟል፡፡
አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያው በታሪኩ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን መንገደኛ ያስተናገደው እ.ኤ.አ በ2019 እንደነበር ያስታወሰው ዘገባው፤ በአመቱ 86.4 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገዱንም አክሎ ገልጧል፡፡
በአመቱ በአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያው ከተስተናገዱ አለማቀፍ መንገደኞች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ህንዳውያን ሲሆኑ፣ 4.2 ሚሊዮን ያህል የህንድ መንገደኞች በጣቢያው መስተናገዳቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡


Read 1209 times